የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

በሩዝ ልማት የተሰማሩ የምዕራብ ወለጋ ዞን አርሶ አደሮች ተጨማሪ ገቢ እያገኙ ነው

Aug 12, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ጊምቢ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ) ፡-በምዕራብ ወለጋ ዞን በሩዝ ልማት የተሰማሩ አርሶ አደሮች ምርትና ምርታማነታቸውን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ተጨማሪ ገቢ እያገኙ መሆናቸውን አስታወቁ።

በኢትዮጵያ በግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ ውስጥ ከተያዙት ስትራቴጂካዊ የሰብል ልማቶች መካከል የሩዝ ልማት አንዱ ነው።

በኦሮሚያ ክልል በሚገኘው የምዕራብ ወለጋ ዞን የሚገኙ በርካታ ወረዳዎችም ለሰብል ልማት ምቹ የሆነ የአየር ፀባይ፣ ለም አፈርና በቂ የውሃ ሀብት ያላቸው በመሆኑ ለሩዝ ምርት ተስማሚ እንደሆኑ ይነገራል።

ቀደም ሲል በአካባቢው አርሶ አደሮች በዋናነት በበቆሎ፣ በጤፍና በቡና ልማት ላይ ብቻ ትኩረት አድርገው ይሠሩ የነበረ ቢሆንም፤ በቅርብ ዓመታት ውስጥ መንግሥትና የግብርና ባለሙያዎች ባደረጉት የተቀናጀ ድጋፍ የሩዝ ሰብል ማልማት ተስፋ ሰጪ ሆኗል።

በአጠቃላይ በዞኑ እየተካሄደ ያለው የሩዝ ልማት እንቅስቃሴ አርሶ አደሩን ከራስ-አልፎ-ለገበያ አምራችነት ያሸጋገረና የኢኮኖሚ እድገቱን የሚያፋጥን ቁልፍ ዘርፍ እየሆነ መጥቷል።

ከሩዝ አምራች አርሶ አደሮች አንዱ የሆኑት የጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ነዋሪው አቶ ኑሬ ጀማል፤ ከዚህ ቀደም ባካበቱት ልምድ በመጠቀም በዘንድሮው የመኸረ አዝመራ ግማሽ ሄክታር መሬት በሩዝ ሰብል መሸፈናቸውን ተናግረዋል።

አርሶ አደሩ በሩዝ ልማቱ ውጤታማ ለመሆን አስፈላጊውን እንክብካቤ እያደረጉ መሆናቸውን ገልጸው፤ ይህም የምግብ ዋስትናቸውን ከማረጋገጡ ባሻገር ምርቱን ለገበያ ለማቅረብ አቅደው እየሰሩ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።

የመነሲቡ ወረዳ ነዋሪው አርሶ አደር ፈቀደ ጆቴ ደግሞ ቀደም ሲል በቡና ልማት ላይ ብቻ ያተኩሩ እንደነበር አስታውሰዋል።

አሁን ላይ ግን በኢንሼቲቭ መልክ እየተካሄደ ባለው የሩዝ ልማት መሳተፋቸው የተሻለ ተጠቃሚ እንዳደረጋቸው ተናግረዋል።

በኩታ ገጠም ባለሙት የሩዝ ማሳ ላይ የተሻለ ምርት ለማግኘት የግብርና ባለሙያዎችን ምክር በመከተል አስፈላጊውን እንክብካቤ እያደረጉ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

አርሶ አደር ዱሌ ካሚሶ በበኩላቸው፤ ከጅምሩ ማሳቸውን በደንብ በማረስና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀማቸው የሩዝ ሰብላቸው በጥሩ ቁመና ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የሩዝ ሰብሉ ደርሶ ወደ ጎተራ እስከሚገባ ድረስ ተገቢውን እንክብካቤና ጥበቃ ማድረጋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም አርሶ አደሩ ገልጸዋል።


በዘንድሮው የመኸር ልማት የሩዝ አምራችነትን ለማስፋፋት በተሰራው ሥራ ከ175 ሺህ 749 ሄክታር በላይ መሬት በሰብሉ መሸፈኑንና 7 ሚሊዮን 451 ሺህ ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ የገለጸው ደግሞ የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ነው።

የጽሕፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ፈይሳ ሀምቢሳ እንዳሉት፤ የአርሶ አደሩን ምርታማነት በመጨመር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በሩዝ ልማት ዘርፍ ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑንም አብራርተዋል።

በዞኑ የሩዝ ልማት በአርሶ አደሮች፣ በማህበራትና በኢንቨስተሮች ጥረት እየተካሄደ እንደሚገኝ የጠቆሙት ሃላፊው፤ የሩዝም ሆነ የሌሎች ሰብሎችን ምርታማነት ለማሳደግ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት የመንግሥት ኤሌክትሮኒክ ግዥ ስርዓት ውጤታማነትን አሻሽሏል

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት የመንግሥት ኤሌክትሮኒክ ግዥ ስርዓትንና የወጪ ውጤታማነትን ማ...

Jul 31, 2026

በክልሉ በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል 

ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...

Jul 31, 2026

በአስተዳደሩ በበጀት ዓመቱ ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በመሰብሰብ የነዋሪውን የልማት ጥያቄ ለመመለስ ጥረት ተደርጓል

ድሬደዋ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦ በበጀት ዓመቱ ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በመሰብሰብ የነዋሪውን የልማት ጥያቄ ለመመለስ ጥረት መደረጉን የድሬደዋ አስተዳ...

Jul 20, 2026

በመረጃ የተደገፈ ውሳኔ አሰጣጥ በክልሎች መካከል የተመጣጠነ ልማት ከማረጋገጥ አንጻር ጠንካራ መሰረት እየጣለ ነው

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/2018(ኢዜአ)፦ በመረጃ የተደገፈ ውሳኔ አሰጣጥ በክልሎች መካከል የተመጣጠነ ልማት ከማረጋገጥ አንጻር ጠንካራ መሰረት መጣል መቻሉን የፌ...

Jul 7, 2026