🔇Unmute
መቱ ፣ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ):- በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተደረገላቸው ድጋፍ በዘላቂነት ሠርተው ራሳቸውን እንዲለውጡ የሚያስችል መሆኑን በኢሉባቦር ዞን የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ገለጹ።
በኦሮሚያ ክልል ኢሉባቦር ዞን በየዓመቱ የሚካሄደው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውንና አቅመ ደካማ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ ለመደገፍ ያለመ እንቅስቃሴ ነው።
ይህ የበጎ ፈቃድ ንቅናቄ የመንግሥት፣ የበጎ አድራጊዎችንና የሕዝቡን አቅም አስተባብሮ በመጠቀም በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸውን ሥራዎች ለማከናወን የሚያስችል መድረክ ሆኖ በመሰራት ላይ ይገኛል።
በኢሉባቦር ዞን ከአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች መካከል አካል ጉዳተኛዋ ወይዘሮ ትዕግስት ኦሊቃ፤ ባለፉት ዓመታት የምግብ ሸቀጦችና ሌሎች ጊዜያዊ ድጋፎች ይደረጉላቸው እንደነበር አስታውሰዋል።
ኑሯቸውን የሚመሩት እንጀራ ጋግረው በመሸጥ ቢሆንም፣ ሥራውን በማገዶ እሳት ያከናውኑ ስለነበር ስራው ከባድ እንደነበር ገልጸዋል።
አሁን ግን በክረምቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተበረከተላቸው የኤሌክትሪክ ምጣድ ሥራቸውን በእጅጉ የሚያቀልላቸው መሆኑን በመጠቆም፣ ከዕለት ጉርስ ባለፈ ጠንክረው በመሥራት ራሳቸውን ለመለወጥ ቁርጠኛ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል።
በተመሳሳይ አቶ ለገሠ ዋኬኔ የተሰጣቸውን የወተት ላም መነሻ በማድረግ ከተረጂነት ለመላቀቅ እንደሚተጉ ጠቁመው፣ ላሟን በማርባት በዘላቂነት ራሳቸውን ለመቻልና ለሌሎችም ለመትረፍ ማቀዳቸውን ተናግረዋል።
በተመሳሳይ የዶረኒ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አቶ ጀማል ኑሪ፣ ከአልባሳትና የምግብ ሸቀጦች በተጨማሪ ያገኙት ዘመናዊ የንብ ቀፎ በዘላቂነት ሠርተው የሚለወጡበትን የሥራ ዕድል የሚፈጥርላቸው መሆኑን ገልጸዋል።
ወይዘሮ ሃምዲያ አህመድኑርም በተደረገላቸው የበጎች ድጋፍ መደሰታቸውን ገልጸው፣ ድጋፉ ራሳቸውን ለመለወጥ የሥራ ተነሳሽነት እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል።
በዚህም ጠንክረው በመሥራት ከተረጂነት ለመላቀቅና በቀጣይ ሌሎችን መደገፍ የሚችሉበት ደረጃ ላይ ለመድረስ እንደሚተጉ አብራርተዋል።
የመቱ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘሮ አሾ ኢሳ በበኩላቸው፣ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ችግራቸውን በጊዜያዊነት የሚቀርፍ ብቻ ሳይሆን በዘላቂነት ከተረጂነት የሚወጡበትን የሥራ እድል የሚፈጥርላቸው መሆኑን ገልጸዋል።

የኢሉባቦር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳልካቸው ተፈሪ እንደተናገሩት፤ በዞኑ ድጋፍ የሚሹ ወገኖች የሌሎችን እጅ ከመጠበቅ ወጥተው በዘላቂነት ገቢ የሚያገኙበትን ዕድል መፍጠር ላይ ትኩረት ተደርጓል።
በዚህም ቋሚ የሀብት ድጋፎችን በማቅረብ ሠርተው ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች መትረፍ የሚችሉ አምራች ወገኖች እንዲሆኑ እየተደረገ ነው ብለዋል።
በዚህ መሰረት ዘመናዊ የንብ ቀፎ፣ የኤሌክትሪክ ምጣድ፣ የቁም እንስሳትና ሌሎች ድጋፎች እየተደረጉላቸው መሆኑን ገልጸዋል።
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት የመንግሥት ኤሌክትሮኒክ ግዥ ስርዓትንና የወጪ ውጤታማነትን ማ...
Jul 31, 2026
ድሬደዋ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦ በበጀት ዓመቱ ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በመሰብሰብ የነዋሪውን የልማት ጥያቄ ለመመለስ ጥረት መደረጉን የድሬደዋ አስተዳ...
Jul 20, 2026