🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ውጤታማ የልማትና የአካባቢ ጥበቃ ተግባራት ለአፍሪካ ሀገራት ትልቅ ተሞክሮ መሆናቸውን ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ ጎብኚዎች ገለጹ።
ከቦትስዋና የመጡትና በአዲስ አበባ ለቀናት ጉብኝት ያደረጉት ቲሞቲ ካጎ ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት፣ ኢትዮጵያን ለመጀመሪያ ጊዜ መጎብኘታቸውን ጠቁመው፤ በከተማዋ በተመለከቱት የልማት ተግባራት መደመማቸውን ገልጸዋል።

በቆይታቸው የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክቶችን መጎብኘታቸውን፣ የልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ተግባራቱ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የወንዞቹን የቀድሞ ገጽታ መመልከታቸውን ጠቁመው፣ መሰል የተፈጥሮ ጸጋዎችን ወደ ልዩ የመዝናኛ ስፍራዎች መቀየር እንደሚቻል በአዲስ አበባ የተመዘገበው ውጤት ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
በወንዝ ዳርቻዎች የተከናወኑ የልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ተግባራት ለመናፈሻነትና ለመዝናኛነት ከመዋላቸው ባለፈ፣ ለኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች መጎልበት የተገነቡ ሱቆችና አዳዲስ ሥራ ፈጠራዎች ማካተቱ ትልቅ እርምጃ መሆኑን ተናግረዋል።
ይህም ቁርጠኛ አመራር ካለ ትልልቅ የልማት ተግባራትን በማከናወን ውጤት ማስመዝገብ እንደሚቻል ያሳያል ነው ያሉት።
ይህ የልማት ሥራ የተፈጥሮ ጸጋዎችን እንዴት ወደ ኢኮኖሚ ምንጭነት መቀየር እንደሚቻል ለአፍሪካ ሀገራት ትልቅ ትምህርት እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።
በተጨማሪም የአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ተግባራት በትብብር ሲከናወኑ ምን ያህል ውጤታማ እንደሚሆኑ መታዘባቸውንም ገልጸዋል።

ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያን መጎብኘቷን የተናገረችው ካሜሮናዊቷ ወጣት ስዋዚ ኢቤል-ኤቤል፤ ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣቷ በፊት ስለ ኢትዮጵያ የልማት ተግባራትና ውጤታማነት ግንዛቤ ማግኘቷን አንስታለች።
በአዲስ አበባ ጉብኝቷ ኢትዮጵያ በአስደማሚ የልማት እንቅስቃሴ ላይ እንደምትገኝ መመልከቷንና ይህም ለአፍሪካ ተምሳሌት መሆኑን ጠቅሳ፣ የሕዝቡ እንግዳ ተቀባይነትም ልዩ እና የሚደነቅ ነው ብላለች።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026