የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

ማዕከሉ በምርምር ያወጣቸው የሩዝ ዝርያዎች የዝናብ እጥረትና በሽታን ተቋቁመው ከፍተኛ ምርት እያስገኙ ነው

Oct 12, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ገንዳውኃ፣ መስከረም 30/2019(ኢዜአ)፡-የጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል በምርምር ያወጣቸው የተሻሻሉ የሩዝ ዝርያዎች የዝናብ እጥረት እና በሽታን ተቋቁመው ከፍተኛ ምርት እያስገኙ መሆኑን በምዕራብ ጎንደር ዞን የመተማ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለጹ።

​የጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል በመተማ ንዑስ ማዕከል እያካሄደ ያለውን የሩዝ ዘር ብዜትና የሰብል ልማት ለአርሶ አደሮች፣ አመራሮችና የግብርና ባለሙያዎች ዛሬ አስጎብኝቷል።


በልማቱ እየተሳተፉ ያሉት ​የመተማ ወረዳ አርሶ አደር ጋሻው ሙሀመድ እንደገለጹት፤ ማዕከሉ ያወጣቸው "ፎገራ-1" እና "አዝመራ" የተባሉ የተሻሻሉ የሩዝ ዝርያዎች ለአካባቢው ስነ ምህዳር ተስማሚ ናቸው።

የተሻሻሉ የሩዝ ዝርያዎቹ የዝናብ እጥረትን፣ በሽታን እና ሌሎች ችግሮችን ተቋቁመው ከፍተኛ ምርትየሚያስገኙ በመሆኑ

የምግብ ዋስትናቸውን ለማረጋገጥ እንዳስቻላቸው ተናግረዋል።

ሌላኛው አርሶ አደር አህመድ ይመር በበኩላቸው፣ የሩዝ ልማቱ ከቤት ውስጥ የምግብ ፍጆታ ባለፈ ለገበያ በማቅረብ ተጨማሪ ሃብት ለመፍጠር እያስቻላቸው መሆኑን ተናግረዋል።

በጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል የመተማ ንዑስ ማዕከል አስተባባሪና ሰብል ተመራማሪ አቶ ግዛት አዱኛ፣ ማዕከሉ አዳዲስ የሰብል ዝርያዎችና የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅና በማስተዋወቅ ሥራ ላይ ማተኮሩን ገልጸዋል፡፡

በተለይም በአንድ ሄክታር እስከ 55 ኩንታል ምርት የሚሰጡት የፎገራ-1 እና አዝመራ የተባሉ የሩዝ ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩ በማሰራጨት በምግብ ራሱን ከመቻል ያለፈ ለገበያ በማቅረብ ትርፍ ምርት እንዲያመርት ለማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።

​የምዕራብ ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ጤናው ፈንታሁን በበኩላቸው እንዳሉት፣ በዞኑ የተሻሻሉ የሩዝ ዝርያዎችን በማስፋፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየተሰራ ያለው ሥራ ውጤት አምጧል።


የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ሀገራዊ ቀጣይ የልማት ግቦችን ለማሳካት ሁሉም ዜጋ በተደመረ አቅምና ትብብር መስራት አለበት-ምሁራን

ጋምቤላ፤ መስከረም 29/ 2019 (ኢዜአ)፡- ሀገራዊ ቀጣይ የልማት ግቦችን ለማሳካት ሁሉም ዜጋ በተደመረ አቅምና በትብብር ሊሰራ ይገባል ሲሉ የጋምቤላ ዩኒቨርሲ...

Oct 10, 2026

በዞኑ በምርት ዘመኑ 28 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ የሚያስችሉ ተግባራት እየተካሄዱ ነው

ባህር ዳር፤ መስከረም 4/2019 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ጎንደር ዞን በመኸር ወቅት ከለማው 641 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ከ28 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰ...

Sep 15, 2026

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026

በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12  ባለሀብቶች ላይ  እርምጃ ተወሰደ

ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...

Aug 14, 2026