የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

የሕዝብን ጥቅም የሚያስቀድም፣ የዜጎችን ክብር የሚጠብቅ እና ተጨባጭ ውጤት የሚያመጣ ሥራ እንሠራለን 

Oct 12, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2019 (ኢዜአ)፦ የሕዝብን ጥቅም የሚያስቀድም፣ የዜጎችን ክብር የሚጠብቅ እና ተጨባጭ ውጤት የሚያመጣ ሥራ እንሠራለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለተከታታይ ሁለት ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን የአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ማጠናቀቁን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።


ከንቲባዋ በመልዕክታቸው በአንደኛው ሩብ ዓመት የከተማዋ ነዋሪዎች በአስተዳደሩ ላይ የጣሉትን እምነት እና የሰጡትን ኃላፊነት በታማኝነት ለመወጣት በተገባው ቃል መሠረት፣ በነዋሪዎች የኑሮ ሁኔታና ተጠቃሚነት ላይ ለውጥ ያመጡ እንዲሁም ለቀጣይ ሥራዎች መሠረት የጣሉ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸው በግምገማው መረጋገጡን ገልጸዋል።

ለተመዘገበው ውጤት በከተማዋ የተፈጠረው የሥራ ትጋት፣ በታማኝነት የማገልገል ባህል፣ በመደመር መርህ በፍጥነት እና በጥራት የመፈጸም ልምድ እንዲሁም ጊዜን ሳያባክኑ ዕቅድን ወደ ተግባር የመቀየር አቅም መሆኑን ጠቁመዋል።

አክለውም፣ ወቅቱ የሚጠይቀውን አደረጃጀት በማሻሻል እና ውጤትን መሠረት በማድረግ አዳዲስ የአመራር ስምሪቶች መከናወናቸውን አብራርተዋል።

በ90 ቀናት ዕቅዱ የክረምት በጎ ፈቃድ፣ የአረንጓዴ ዐሻራ፣ የቤቶች ግንባታ እና የተጎሳቆሉ አካባቢዎችን የማሻሻል ሥራዎች መከናወናቸውን የጠቆሙት ከንቲባዋ፣ የቤት ችግር ያለባቸው እና በልማት ምክንያት ከመኖሪያቸው የተነሱ ዜጎች ንጹሕና ክብራቸውን የሚጠብቁ ቤቶች እንዲያገኙ መደረጉን ገልጸዋል።

ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ነዋሪዎች የኑሮ ጫና ለመቀነስ የማዕድ ማጋራት ሥራዎች መከናወናቸውን እና በክረምት ግንባታ አይከናወንም የሚለውን የቆየ አስተሳሰብ በመቀየር በርካታ ፕሮጀክቶችን ማከናወን መቻሉን አስታውቀዋል።


በትራንስፖርት መሠረተ ልማት ዘርፍ አራት ትላልቅ የመኪና ማቆሚያ እና ተርሚናል ማዕከላት ወደ ሥራ መግባታቸውን፣ አዳዲስ የብስክሌት እና የእግረኛ መንገዶች፣ የውኃ ማስወገጃ እና የፍሳሽ መስመሮች በመገንባታቸው በክረምት ወቅት የሚከሰቱ የጎርፍ አደጋዎችን እና የሰው ሕይወት ማጣትን መቀነስ ተችሏል ብለዋል።

የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋትም በሰባት የገበያ ማዕከላት ሰፊ የምርት አቅርቦት እንዲገባ መደረጉን እና የቅዳሜ እና እሁድ ገበያዎች ደረጃ መሻሻሉን ገልጸዋል።

የተበታተነ አቅም ራዕይን እንደማያሳካ እና ሀገርንም እንደማይገነባ ያመለከቱት ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ እያንዳንዱ ሠራተኛ በግልጽ የተለየ የሥራ ድርሻ እና ተጠያቂነት ኖሮት በመደመር መርህ ተቀናጅቶ የሚሠራበትን አሠራር ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል።

ከንቲባ አዳነች፣ "የሕዝብን ጥቅም የሚያስቀድም፣ የዜጎችን ክብር የሚጠብቅና ተጨባጭ ውጤት የሚያመጣ ሥራ እንሠራለን!" በማለት ከተማ አስተዳደሩ የሕዝቡ ኑሮ ላይ ለውጥ የሚያመጣ ሥራ ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ሀገራዊ ቀጣይ የልማት ግቦችን ለማሳካት ሁሉም ዜጋ በተደመረ አቅምና ትብብር መስራት አለበት-ምሁራን

ጋምቤላ፤ መስከረም 29/ 2019 (ኢዜአ)፡- ሀገራዊ ቀጣይ የልማት ግቦችን ለማሳካት ሁሉም ዜጋ በተደመረ አቅምና በትብብር ሊሰራ ይገባል ሲሉ የጋምቤላ ዩኒቨርሲ...

Oct 10, 2026

በዞኑ በምርት ዘመኑ 28 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ የሚያስችሉ ተግባራት እየተካሄዱ ነው

ባህር ዳር፤ መስከረም 4/2019 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ጎንደር ዞን በመኸር ወቅት ከለማው 641 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ከ28 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰ...

Sep 15, 2026

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026

በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12  ባለሀብቶች ላይ  እርምጃ ተወሰደ

ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...

Aug 14, 2026