የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

የአፍሪካ ሀገራት የጤናው ስርዓታቸውን ይበልጥ ለማጎልበት ተሞክሮዎችን መጋራትና እርስ በእርስ መማማር አለባቸው

Nov 24, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ህዳር 14/2019 (ኢዜአ)፦የአፍሪካ ሀገራት የጤናው ስርዓታቸውን ይበልጥ ለማጎልበት ተሞክሮዎችን መጋራትና እርስ በእርስ መማማር እንዳለባቸው የዩጋንዳ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄሲካ አሉፖ ገለጹ።

5ኛው ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የሕዝብ ጤና ጉባኤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡

ጉባኤው "የአፍሪካ የጤና ደህንነት እና ሉዓላዊነት፤ ከጤና ጥገኝነትና ተጋላጭነት ወደ ባለቤትነትና ጽናት የሚደረግ ሽግግር" በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

ይህ ዓመታዊ ጉባኤ የአፍሪካ የፖለቲካ መሪዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የሕዝብ ጤና ባለሙያዎች፣ ሳይንቲስቶች፣ የልማት አጋሮች፣ የግሉ ዘርፍ ተወካዮች እና የማኅበረሰብ አንቂዎች በአንድ መድረክ ተገናኝተው በአህጉሪቷ ቅድሚያ በሚሰጣቸው የጤና አጀንዳዎች የሚመክሩበት፣ ሳይንሳዊ ዕውቀቶችን የሚለዋወጡበት እንዲሁም አዳዲስ የፈጠራ መፍትሔዎችን የሚያስተዋውቁበት የትብብር ማዕቀፍ ነው።

በተጨማሪም ገለባኤው ትብብርን ለማጠናከር፣ ምርምርን ለማሳደግ እና የማይበገርና በራስ አቅም ላይ የተመረኮዘየጤና ሥርዓት ለመገንባት የሚያስችሉ አፍሪካ-መር አካሄዶችን ለማጠናከር ሰፊ ዕድል ይፈጥራል።

የዩጋንዳ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄሲካ አሉፖ ዩጋንዳ ከአራት አስርት ዓመታት በላይ ታላላቅ የሕዝብ ጤና ፈተናዎችን መጋፈጧን ገልጸዋል፡፡

ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ፣ ተከታታይ የኢቦላ ወረርሽኞች፣ ማርበርግ፣ ኮቪድ-19 እና ኤምፖክስ (mpox) የመሳሰሉ በሽታዎችንም ለአብነት አንስተዋል፡፡

እነዚህ ወረርሽኞች ሕዝባቸውንና ተቋሞቻቸውን በተለያዩ መንገዶች መፈተናቸውን አንስተው፤ ዩጋንዳ በእነዚህ አስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ ሕዝቧንና አንድነቷን በማስጠበቅ እንዲሁም መውጫ መንገድ የማግኘት ተግባራትን በብቃት መወጣቷን ተናግረዋል፡፡

" የአንዲት ሀገር ጥንካሬ የሚለካው ቀውስ አለመኖር ሳይሆን፣ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ሕዝቧንና አንድነቷን ጠብቆ ማለፍ ነው " ብለዋል፡፡

ይህም የአንዲት ሀገር ጤና ከሰላሟ እና ከደኅንነቷ ተነጥሎ ሊታይ እንደማይችል እንዳስተማራቸው ገልጸዋል፡፡

ትብብሮች ሀገራት በግልጽ እንዲነጋገሩ፣ መረጃ እንዲለዋወጡ እና በአንድነት እንዲቆሙ መሠረት እንደሚጥል ጠቁመዋል፡፡

የአፍሪካ ሀገራት እርስ በርስ መማማር፣ መደጋገፍ እና በራሳቸው አስቸጋሪ ተሞክሮዎች የገነቧቸውን አቅሞች መጋራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የአፍሪካ የወደፊት ዕጣ ፈንታ አንዲት ሀገር ብቻዋን በምታደርገው እንቅስቃሴ እንደማይረጋገጥ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በመሆኑም ሕዝቦች፣ ተቋማት እና ሀገራት መካከል ያለውን ትስስር ማጠናከር መቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአርባ ምንጭ ግብርና ምርምር ማዕከል የቀረቡ የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎች የአርሶ አደሩን ምርትና ገቢ እያሳደጉ ነው

አርባ ምንጭ፤ ሕዳር 7/2019 (ኢዜአ)--የአርባ ምንጭ ግብርና ምርምር ማዕከል ምርታማነትን የሚጨምሩ የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎችን በማላመድና የግብርና ቴክኖሎጂ...

Nov 17, 2026

ታሪክ የማይዘነጋው ክህደት እና የኢትዮጵያዊያን አኩሪ ጽናት!

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሀገርን ሉአላዊነት ከመጠበቅ ባለፈ የልማት አጋር በመሆንና በማህበራዊ አገልግሎት በመሳተፍ ህዝባዊነቱን በተግባር ያረጋገጠ ሰራዊት ...

Nov 3, 2026

በክልሉ የመልማት አቅሞችን በመጠቀም የህዝቡን ኑሮ ለማሻሻል የሚከናወኑ ተግባራት ይጠናከራሉ

ቁሊቶ ፤ ጥቅምት 15/2019 (ኢዜአ) ፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመልማት አቅሞችን በመጠቀም ዘላቂ ሰላምና ልማትን በማፋጠን የህዝቡን ኑሮ ለማሻሻል የሚከና...

Oct 26, 2026

በሲዳማ ክልል የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ ስራዎች ይጠናከራሉ

ሀዋሳ፤ ጥቅምት 3 /2019 (ኢዜአ)፦በሲዳማ ክልል የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ ሥራዎች እንደሚጠናከሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር መሳ...

Oct 14, 2026