የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

የኢንዱስትሪው ዘርፍ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከግብርና የላቀ የጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ድርሻ መያዝ ችሏል

Nov 27, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፣ ህዳር 17/2019 (ኢዜአ)፦የኢንዱስትሪው ዘርፍ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከግብርና የላቀ የጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ድርሻ መያዙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ዛሬ 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በመደበኛ ጉባኤው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ስብሰባ ያቀረቡትን የ2019 ዓ.ም የመንግሥት ዕቅድ መነሻ በማድረግ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማብራሪያቸው እንደገለጹት የኢንዱስትሪው ዘርፍ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከግብርና የላቀ የጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ድርሻ መያዝ ችሏል።

ለረጅም ጊዜ ሲነገር የቆየው የኢኮኖሚ ሽግግርና ግብርና መር ኢኮኖሚን ወደ ኢንዱስትሪ የመቀየር ጥረት በዘንድሮው ዓመት መጠነኛ ሽግሽግ ማሳየቱን አመልክተዋል።

በዘንድሮው ዓመት ወደ 9 ነጥብ 9 በመቶ ዕድገት እንደሚያስመዘግብ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ያለው ድርሻ 33 ነጥብ 8 በመቶ ነው ብለዋል።

ማኑፋክቸሪንግንና ኮንስትራክሽንን ጨምሮ በዘንድሮው ዓመት 12 ነጥብ 3 በመቶ ዕድገት እንደሚያስመዘግብ የሚጠበቅ ሲሆን የጂዲፒ (ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት) ድርሻው 31 ነጥብ 8 በመቶ በመሆን ከግብርና የላቀ ድርሻ ይዟል ሲሉ ተናግረዋል።

በዘንድሮው ዓመት 7 ነጥብ 7 በመቶ ዕድገት እንደሚያመጣ የሚጠበቅ ሲሆን፣ በአሁኑ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ያለው ድርሻ 31 ነጥብ 4 በመቶ በመሆን በኢኮኖሚው ውስጥ ሦስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጡን አስታውቀዋል።

የዘንድሮው የመንግሥት ዕቅድ በተቀመጠው ልክ ሲሳካ በዚያው ልክ በዘርፎች መካከል ያለው የኢኮኖሚ ሽግሽግ እየሰፋ እንደሚሄድ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአርባ ምንጭ ግብርና ምርምር ማዕከል የቀረቡ የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎች የአርሶ አደሩን ምርትና ገቢ እያሳደጉ ነው

አርባ ምንጭ፤ ሕዳር 7/2019 (ኢዜአ)--የአርባ ምንጭ ግብርና ምርምር ማዕከል ምርታማነትን የሚጨምሩ የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎችን በማላመድና የግብርና ቴክኖሎጂ...

Nov 17, 2026

ታሪክ የማይዘነጋው ክህደት እና የኢትዮጵያዊያን አኩሪ ጽናት!

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሀገርን ሉአላዊነት ከመጠበቅ ባለፈ የልማት አጋር በመሆንና በማህበራዊ አገልግሎት በመሳተፍ ህዝባዊነቱን በተግባር ያረጋገጠ ሰራዊት ...

Nov 3, 2026

በክልሉ የመልማት አቅሞችን በመጠቀም የህዝቡን ኑሮ ለማሻሻል የሚከናወኑ ተግባራት ይጠናከራሉ

ቁሊቶ ፤ ጥቅምት 15/2019 (ኢዜአ) ፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመልማት አቅሞችን በመጠቀም ዘላቂ ሰላምና ልማትን በማፋጠን የህዝቡን ኑሮ ለማሻሻል የሚከና...

Oct 26, 2026

በሲዳማ ክልል የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ ስራዎች ይጠናከራሉ

ሀዋሳ፤ ጥቅምት 3 /2019 (ኢዜአ)፦በሲዳማ ክልል የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ ሥራዎች እንደሚጠናከሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር መሳ...

Oct 14, 2026