የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ(ዶ/ር) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመንገድ ደህንነት ፈንድ የቦርድ አባል ሆነው ተሾሙ

Mar 12, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 03/2017(ኢዜአ)፦ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ(ዶ/ር) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመንገድ ደህንነት ፈንድ የቦርድ አባል ሆነው ተሾመዋል፡፡

ኢትዮጵያ ሀገራዊ የመንገድ ደህንነት ስትራቴጂ በመቅረፅና የመንገድ ደህንነት ትምህርት በስርዓተ ትምህርት ውስጥ እንዲካተት በማድረግ የወሰደችው እርምጃ የመንገድ ደህንነትን ለማስፈን ያላትን ቁርጠኝነት ማሳያ መሆኑ ለሚኒስትሩ በተጻፈ ደብዳቤ ተገልጿል፡፡

በኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ስራዎች የተገነቡ ምቹ የብስክሌትና የእግረኛ መንገዶች እንዲሁም የተሻሻሉ የመንገድ ትስስር ስራዎች እንደ ሀገር የትራንስፖርት መሰረተ ልማት ቅንጅትን የሚያሳድጉ እንደሆኑ ከትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።

የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ኢትዮጵያ በመንገድ ደህንነት ላይ ያላትን ቁርጠኝነትና የምታደርገውን ጥረት በመገንዘብና እውቅና በመስጠት ሚኒስትሩ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመንገድ ደህንነት ፈንድ ስር የባለአደራዎች ቦርድ አባል ሆነው መሾማቸውን አሳውቋል፡፡

ይህም ኢትዮጵያ ልምዷን ለሌሎች ሀገራት እንድታጋራና ከመላው ዓለም በመንገድ ደህንነት ላይ የተሻሉ ተሞክሮዎችን እንድታገኝ መልካም አጋጣሚ የሚፈጥር እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመንገድ ደህንነት ፈንድ እ.ኤ.አ ሚያዝያ 2018 የተመሠረተ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ጠቀሜታ ላላቸው ፕሮጀክቶች ተጨማሪ ገንዘብ የማሰባሰብ እና የመደገፍ ስራን የሚሰራ ዓለማቀፍ ድርጅት ነው፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026

በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል

ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...

Sep 7, 2026

በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...

Aug 31, 2026