የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

በክልሉ የማዕድን ሀብት ልማት ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል እየፈጠረና ከፍተኛ የገቢ አቅም እየሆነ ነው

Jun 10, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ባህር ዳር፤ ሰኔ 2/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል የማዕድን ሀብት ልማት ዘርፉ በጥናትና ምርምር በመታገዙ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል እየፈጠረና ከፍተኛ የገቢ አቅም እየሆነ መምጣቱን የክልሉ ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ ገለጸ።

ቢሮው በክልሉ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የሥነ ምድር ጥናትና ካርታ ስራ እንዲሁም የማዕድን ፍለጋና ክምችት ግመታ ጥናት የውል ፊርማ ስነ-ስርዓት አካሂዷል።

የቢሮ ኃላፊው ሀይሌ አበበ በመድረኩ እንደገለፁት፤ በክልሉ የማዕድን ሀብት ልማቱን በጥናትና ምርምር በማስደገፍ በተሰራ ስራ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል እየፈጠረና ከፍተኛ የገቢ አቅም እየሆነ ነው።

በዚህም በክልሉ የግራናይት፣ የማርብል፣ የጅብሰም፣ የወርቅ፣ የብረትና ሌሎች ማዕድናት በጥናት መለየታቸውን አብራርተዋል።

ዘርፉን በጥናትና ምርምር በመለየትና በማልማት ተኪ ምርቶችን በማምረት የውጭ ምንዛሬን ለማሳደግ መዋላቸውንም ገልፀዋል።ዘርፉ ለስራ ዕድል ፈጠራና ኢንቨስትመንቱ እንዲነቃቃ በማድረግ በኩል ተጨባጭ ለውጥ መመዝገቡን አመልክተዋል።

በቀጣይም የዘርፉን የመልማት አቅም በጥናትና ምርምር ውጤቶች ላይ በመመርኮዝ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ በቅንጅት ይሰራል ነው ያሉት።

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ትብብር ምክትል ፕሬዚዳንት ተወካይ ውለታው መኩሪያ (ዶ/ር) በበኩላቸው እንደገለጹት፤ ዩኒቨርሲቲው የማዕድን ልማትን በምርምር እያገዘ ይገኛል።


በምርምር ላይ መሰረት ያደረገ የሃብት ፍለጋ ስራ በትብብር መከናወኑ ዘላቂ ዕድገትን ለማስመዝገብ ያስችላል ብለዋል።

የማዕድን ሃብት ልማት ስራው ምርምርና እውቀትን መሰረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑ የሚበረታታ መሆኑን የገለፁት ደግሞ የወሎ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት ሃዋ ወሌ (ዶ/ር) ናቸው።


በክልሉ ያሉትን የማዕድን ሀብቶች በእውቀት ለይቶ ለማልማት በሚደረገው ጥረት ዩኒቨርሲቲው በትብብር እየሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የውል ስምምነቱ የተካሄደው ከባህር ዳር፣ ጎንደር፣ ወልዲያ፣ ወሎ፣ ደብረ ብርሃን እና ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ነው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026

በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል

ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...

Sep 7, 2026

በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...

Aug 31, 2026