የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

የዕዳ ሽግሽግ ድርድሮችን ጨምሮ ሌሎች ተጓዳኝ የአሰራር ማዕቀፎችን በአፋጣኝ ማጠናቀቅ ይገባል

Apr 27, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 18/2017(ኢዜአ)፦ የዕዳ ሽግሽግ ድርድሮችን ጨምሮ ሌሎች ተጓዳኝ የአሰራር ማዕቀፎችን በአፋጣኝ በማጠናቀቅ ቀልጣፋ ሂደትን መከተል እንደሚገባ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ(ዶ/ር) ገለጹ።

በዋሽንግተን ዲሲ አየተካሄደ ካለው የዓለም ባንክ ግሩፕ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ዓመታዊ የፀደይ ወቅት ስብሰባ ጎን ለጎን የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በዓለም አቀፉ የሀገራት የዕዳ ውይይት ላይ ተሳትፋለች።

ስብሰባው በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት(አይኤምኤፍ) ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ እና የዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት አጃይ ባንጋ እንዲሁም በወቅቱ የቡድን 20 ሊቀመንበር በሆነችው ደቡብ አፍሪካ በጋራ የተመራ ነው።

ስብሰባው በቡድን 20 የጋራ ማዕቀፍ የዕዳ ሽግሽግ ሂደት የሚገኝበትን ደረጃ በመገምገም የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ መወሰድ የሚገባቸውን እርምጃዎች አመላክቷል።


የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ(ዶ/ር) በመድረኩ እንደተናገሩት የዕዳ ማዕቀፉ ረጅም ጊዜ ቢወስድም ያለው ፋይዳ ወሳኝ ነው።

ይህም በዛምቢያ፣ ጋና እና አሁን ደግሞ በኢትዮጵያ የተደረጉት የተሳኩ የዕዳ ሽግሽግ ጥረቶች ማሳያ እንደሆኑ ጠቅሰዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው አክለው በተበዳሪው ሀገር እና በአበዳሪዎች ኮሚቴ መካከል ባለው የመርህ ስምምነት መሰረት የብድር አያያዝ ውሎችና ሁኔታዎችን ይፋ በማድረግ ግልፅ አሰራርን የበለጠ ማጎልበት እንደሚገባ አመልክተዋል።

በተጨማሪም ከመርህ ስምምነት ጀምሮ ከአበዳሪ ሀገራት ጋር የሁለትዮሽ ስምምነትና የመግባቢያ ሰነዶችን በመፈራረም ፈጣንና ቀልጣፋ ሂደት በማመቻቸት አላስፈላጊ መዘግየቶችን መቀነስ ተገቢ መሆኑን በአጽንኦት አንስተዋል።

ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በማርች 2025 ከአበዳሪዎች ጋር በመርህ ደረጃ መስማማቷ የሚታወስ ሲሆን እ.አ.አ. በጁን 2025 የመግባቢያ ሰነዱ ዝግጅት እንደሚጠናቀቅ የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026

በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል

ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...

Sep 7, 2026

በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...

Aug 31, 2026