የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ዘርፉ ከፍተኛ ሚና አለው-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

Jun 11, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 3/2017(ኢዜአ)፦በአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ዕድገትን ለማምጣት እና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ዘርፉ ከፍተኛ ሚና አለው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡


አቶ ተመስገን፥በዛሬ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም አመራር ዐቢይ ኮሚቴ አምስተኛ መደበኛ ስብሰባ ማካሄዳቸውን ገልጸዋል።


በውይይቱ ፥በመጀመሪያ ዙር ወደ መሶብ የአንድ ማዕከል አግልግሎት የገቡ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ እና በሁለተኛው ዙር ለመግባት ዝግጅት ያጠናቀቁ ተቋማትን ቅድመ ዝግጅትን ተመልክተናል ብለዋል፡፡


በተጨማሪም የሁሉም ክልሎች እና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች መሶብን ለማስጀመር እያከናወኑ የሚገኙትን የቅድመ ዝግጅት እንቅስቃሴ ሪፖርት ተገምግሟል፡፡


በመሆኑም በመጀመሪያ ዙር ወደ መሶብ የገቡ ተቋማት በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት ቀልጣፋ አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ማየታቸውንም እንዲሁ፡፡


በቀጣይም በሁለተኛ ዙር ወደ መሶብ የሚገቡ ተቋማት እና በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች የሚከናወኑ ተግባራት እንዴት መሰራት እንዳለባቸዉ እና ለተግባራዊ እንቅስቃሴያቸውም አቅጣጫ ተቀምጧል ነው ያሉት፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026

በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል

ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...

Sep 7, 2026

በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...

Aug 31, 2026