
ደብረ ብርሃን ፤ሐምሌ 17/2017(ኢዜአ)፦ በደብረ ብርሃን ከተማ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ሰላምን ከማጽናት ጎን ለጎን ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ የልማት ስራዎች መከናወናቸውን የከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት አስታወቀ።
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።
የምክር ቤቱ ዋና አፈ-ጉባዔ አቶ መንግስቱ ቤተ እንደገለጹት በከተማ አስተዳደሩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በተከናወኑ የሰላምና የልማት ስራዎች አበረታች ውጤት ተመዝግበዋል።
ሰላምን ከማጽናት ጎን ለጎንም የኮሪደር ልማትን ጨምሮ ሌሎች በተከናወኑ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ህብረተሰቡ ተጠቃሚ መሆኑን ጠቅሰዋል ።
በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በተከናወኑ ተግባራትም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ነዋሪዎች የመኖሪያ ቤት ተገንብቶ ርክክብ መደረጉን አውስተዋል ።
ሌሎች እየተካሄዱ ያሉ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃና የቢሮ ህንፃ ግንባታ ስራዎች በአዲሱ በጀት ዓመት ለማጠናቀቅ ክትትል እንደሚደረግ አመላክተዋል።
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት በበኩላቸው እንደገለጹት አስተዳደሩ ማህበረሰቡን በማስተባበር ያከናወናቸው ሰላምን የማጽናትና ልማትን የማረጋገጥ ስራዎች ስኬታማ ነበሩ።
የኮሪደር ልማት፣ የመብራትና የውሃ መስመር ዝርጋታ፣ የውስጥ ለውስጥ መንገድና ሌሎች ኢንቨስትመንትን የማስፋፋት ስራዎችን በውጤታማነት መተግበር መቻሉን ተናግረዋል።
በበጀት ዓመቱ ለ22ሺህ ወጣቶች የስራ እድል መፍጠር መቻሉን ጠቁመው ለስራ እድል ተጠቃሚዎችም የመስሪያና የመሸጫ ቦታ፣ የብድርና ሌሎች ድጋፎች መደረጋቸውን ጠቅሰዋል።
የከተማው ማህበረሰብም ለተከናወኑ የልማት ስራዎች ከ245 ሚሊዮን ብር በላይ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አስታውቀዋል።
ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...
Sep 11, 2026
ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...
Sep 10, 2026
ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...
Sep 7, 2026
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...
Aug 31, 2026