የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

በክልሉ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትን ስኬታማ ለማድረግ የሚያስችል የግብዓት አቅርቦት ተከናውኗል

Nov 28, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዳማ ፤ ሕዳር 19/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትን ስኬታማ ለማድረግ የሚያስችል የግብዓት አቅርቦት በወቅቱ መከናወኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ ገለጸ።

የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ በሪሶ ፈይሳ ለኢዜአ እንደገለፁት፤ በዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ከ4 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት ለመሸፈን ርብርብ እየተደረገ ይገኛል።

ይህም በክልሉ በምግብ ራስን ለመቻል ከተቀረጹ ኢንሼቲቮች መካከል መሆኑን ያነሱት ኃላፊው ተግባሩን ለማሳካትም ግብዓት እና ቴክኖሎጂዎች ለአርሶ አደሮች መሰራጨታቸውን ተናግረዋል።


ባለፉት ዓመታት በክልሉ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የውሀ አማራጮችን በመጠቀምና ወቅትን ሳይጠብቁ ለማምረት ለመስኖ ልማት ትኩረት መሰጠቱን ገልጸዋል።

ለአብነትም ባለፈው ዓመት ሁለት ሚሊዮን ሄክታር የሚጠጋ መሬትን በበጋ መስኖ ስንዴ በማልማት የተሻለ ምርት መገኘቱን ጠቁመዋል።

ካለፈው ዓመት የተገኘውን ልምድ በመጠቀም በዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ከ4 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ርብርብ መደረጉን ተናግረዋል።

በእስካሁኑ ልማትም አንድ ነጥብ 9 ሚሊዮን ሄክታር መሬት መዘጋጀቱንና የምርት ማሳደጊያ ግብዓትና ምርጥ ዘርም በወቅቱ አርሶ አደሩ ጋር መድረሱን ገልጸዋል።


ለመስኖ ልማቱም ከ3 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ መቅረቡንና ከምርጥ ዘር ድርጅትና ዘር ከሚያባዙ አርሶ አደሮች ጋር ትስስር በመፍጠር የስንዴ ምርጥ ዘር እየቀረበ ይገኛል ብለዋል።

የበጋ መስኖ ስንዴ ልማቱን ለማሳካትም የአፈር ለምነትንና እርጥበትን የሚያሻሽሉ የተፈጥሮ ማዳበሪያን በስፋት አርሶ አደሩ እንዲጠቀም ቀደም ብሎ ግንዛቤ መሰጠቱን አክለዋል።


የዘንድሮውን የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት አብዛኛውን በኩታ ገጠም የእርሻ ስነ ዘዴ ለማልማት መታቀዱንና የዝግጅት ስራውን እስከ ታህሳስ ወር መጨረሻ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው ብለዋል።

ለዚህም ከክልል ጀምሮ በዞንና በወረዳ ያሉ አመራሮች፣ የዘርፉ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ክትትልና ሙያዊ ድጋፍ እያደረጉ መሆኑንም አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026

በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል

ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...

Sep 7, 2026

በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...

Aug 31, 2026