🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ህዳር 21/2018(ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ ከተማ የኢንዱስትሪ ምርታማነትን በማሳደግ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለመተካት ትኩረት መሰጠቱን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤና ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር ዓባይ የመዲናዋን የአምራች ኢንዱስትሪ የስራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
በምልከታው ወቅት ከንቲባ አዳነች እንደገለጹት፤ የአምራች ኢንዱስትሪ ምርታማነትን ለማጎልበት ቀጣይነት ያለው የማበረታቻ ድጋፍና ክትትል እየተደረገ ነው።
በኢንዱስትሪዎች የተፈጠረው ከፍተኛ መነቃቃትም በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ስራ የጀመሩ አምራቾችን ወደ ኢንዱስትሪ ማሸጋገር ያስቻለ ስኬት መመዝገቡን ተናግረዋል።
በዚህም በተኪ የኢንዱስትሪ አቅም በማሳደግ ከሀገር ውስጥ ገበያ ባሻገር ጥራትና ብዛት ያላቸው ምርቶችን ለውጭ ገበያ ማቅረብ ያስቻለ አበረታች ውጤት መመዝገቡን አስረድተዋል።
በአዲስ አበባ በሀገር ውስጥ የኢንዱስትሪ ምርት የተገነቡ የኮሪደር ልማት መሠረተ ልማቶችም የራስን የምርት ውጤት የመጠቀም ባህል እያደገ መምጣቱን አመላካች እንደሆነም አብራርተዋል።
በቀጣይም ከውጭ የሚገቡ የኢንዱስትሪ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት አምራቾች በሀገር ሁለንተናዊ የዕድገት ጉዞ ገንቢ ሚናቸውን እንዲወጡ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር ዓባይ፤ በመዲናዋ ከሚገኙ ኢንዱስትሪዎች አብዛኛዎቹ በተኪ ምርት የተሰማሩ ናቸው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ታምርት ሀገር አቀፍ ንቅናቄ በአዲስ አበባ ከተማ በአምራች ኢንዲስትሪ ዘርፍ ለተሰማሩ አምራቾች ከፍተኛ መነቃቃት ጉልህ አስተዋጽኦ መፍጠሩን ገልጸዋል።
በቀጣይም አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚያጋጥማቸውን የመስሪያ ቦታ ጥበትና ተያያዥ ጉድለቶች ተገቢውን ምላሽ በመስጠት የምርታማነት አቅምን ለማሳደግ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
በከተማ አስተዳዳሩ የስራ ኃላፈዎችም በብረታ ብረት፣ በጨርቃ ጨርቅ፣ ግንባታ ማሽነሪና ሌሎች አምራቾችን የሥራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
ባህር ዳር፤ ሰኔ 2/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል የማዕድን ሀብት ልማት ዘርፉ በጥናትና ምርምር በመታገዙ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል እየፈጠረና ከፍተኛ የገቢ...
Jun 10, 2026
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 1/2018 (ኢዜአ)፦ ህዝባችን ለአገልግሎት ፍለጋ ጊዜና ገንዘቡን ሳያባክን ሃብቱን ለልማት እንዲያውል የምናደርገውን ጥረት አጠናክረን እንቀጥ...
Jun 9, 2026
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 19/2018 (ኢዜአ)፦ የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ መመረቅ ፍትሐዊና ሚዛናዊ የመሠረተ ልማት ዝርጋታን የሚያረጋግጥ መሆኑን ጠቅላ...
May 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/2018 (ኢዜአ)፡- ቱሪዝም የኢኮኖሚያችን አንዱ ምሰሶ እንደመሆኑ የሀገራዊ ዕድገታችንን የወደፊት አቅጣጫ እየቀረጸ ያለ ዘርፍ መሆኑ...
Apr 20, 2026