🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ሕዳር 21/2018 (ኢዜአ)፡-የክረምት ወቅት ጥገና ሲደረግለት የሰነበተው ወንጂ ስኳር ፋብሪካ ከነገ ሕዳር 22 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሸንኮራ አገዳ በመፍጨት ስኳር የማምረት ሥራውን ይጀምራል።
ሸንኮራ አገዳ ወደ ፋብሪካው የሚያጓጉዙ ማሽነሪዎች እና የፋብሪካው የጥገና ሥራ መጠናቀቁን የወንጂ ስኳር ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ እዩኤል ለላንጎ አረጋግጠዋል።
በሌላ በኩል ስኳር ለማምረት የሚያስችሉ ሸንኮራ አገዳዎች ዛሬ እንደተቆረጡ ለኢዜአ ገልጸዋል።

በዲዛይን ካፓሲቲው መሠረት የፋብሪካው በቀን ሸንኮራ አገዳ የመፍጨት ዐቅም 6 ሺህ 250 ቶን መሆኑን ገልጸው፥ ያለውን የሸንኮራ አገዳ አቅርቦትና ሌሎች ምክንያቶች ታሳቢ በማድረግ በቀን 4 ሺህ 890 ቶን ሸንኮራ አገዳ በመፍጨት ሥራውን ይቀጥላል ብለዋል።
በዓመት 601 ሺህ 574 ነጥብ 25 ቶን ሸንኮራ አገዳ በመፍጨት 70 ሺህ 239 ነጥብ 8 ቶን ስኳር እንደሚያመርትም አስገንዝበዋል።
ፋብሪካው በሙሉ ዐቅሙ ሸንኮራ አገዳ መፍጨት እንዲችል በአርሶ አደር ማሳ ተጨማሪ የሸንኮራ አገዳ ማሳ ለማልማት ዕቅድ ተይዞ እየተሠራ መሆኑንም አስታውቀዋል።
የሸንኮራ አገዳዎችን ዝርያ የማሻሻል፣ሸንኮራ አገዳ የመፍጨት፣ ስኳር የማምረት ዐቅምና የጨመቃ ሂደት ላይ ምርታማነትን የሚያሳድጉ ሥራዎች በጥገና ወቅት መከናወናቸውን ጠቅሰዋል።
ለዘንድሮው ስኳር የማምረት ሥራ በአማካይ 13 ነጥብ 9 በመቶ የስኳር ይዘት ያለው የሸንኮራ አገዳ ዝርያ ለፋብሪካው እንደሚቀርብም አመላክተዋል።
ፋብሪካው በበጋው ወቅት ሸንኮራ አገዳ በመፍጨት ስኳር የሚያመርት ሲሆን፤ በቀሪዎቹ ወራት በሚኖረው ዝናብና ተፈጥሯዊ ሁኔታ ስለማያመርት ጥገና እንደሚደረግለት ይታወቃል።
ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...
Sep 11, 2026
ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...
Sep 10, 2026
ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...
Sep 7, 2026
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...
Aug 31, 2026