የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

ድሬደዋን ለመኖሪያ እና ለስራ ተመራጭ ከተማ የማድረጉ ጉዞ ተጠናክሮ ይቀጥላል

Dec 3, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

ድሬደዋ፣ ህዳር 23/2018(ኢዜአ)፡- ድሬደዋን ውብና ተመራጭ የመኖሪያ እና የስራ ማዕከል ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የከተማው ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ጀማል ኢብራሂም ተናገሩ።

ኢንጂነር ጀማል ይህን የተናገሩት በከተማዋ እየተካሄዱ በሚገኙ የኮሪደር እና ሌሎች ልማቶች ላይ የህብረተሰቡን ተሳትፎ ለማሳደግ ያለመ ውይይት ላይ ነው።


ኢንጂነር ጀማል በወቅቱ እንደተናገሩት፤ ድሬደዋ ውብና ተመራጭ የስራና የመኖሪያ ማዕከል ለማድረግ እየተከናወኑ የሚገኙ ልማቶች ተጨባጭ ውጤቶች አምጥተዋል።

በተለይም በመጀመሪያ ምዕራፍ በህዝብ ተሳትፎ እየተጠናቀቀ የሚገኘው 11 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ከተማዋን ውብ የስራና ለመኖሪያ ተመራጭ እያደረጋት ይገኛል ብለዋል።

በተጨማሪም በዲጂታል ቴክኖሎጂ በመታገዝ የህዝብን አገልግሎቶች ፈጣንና ቀልጣፋ በማድረግ ስማርት ከተማን የመፍጠሩ ሂደት በስኬት እየተጓዘ መሆኑን በመግለፅ።

እነዚህን ውጤቶች በፈጠራና በፍጥነት በላቀ ደረጃ ለማስፋት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው የማጠናቀቂያ ስራ እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር እና ሌሎች ፕሮጀክቶች ዳር እንዲደርሱ ነዋሪው የድርሻቸውን ሚና እንዲያጠናክር ጠይቀዋል።


በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የንግዱ ማህበረሰብና ነዋሪዎች በበኩላቸው በከተማዋ እየተሰሩ የሚገኙ የኮሪደር ልማቶች የድሬዳዋን ገፅታና ውበት ያረጋገጡ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ከተሳታፊዎቹ መካከል ወይዘሮ እታፈራው አለማየሁ እና መሐመድ ኢድሪስ እንዳሉት ልማቱ የሚፈለገውን ውጤት እንዲያስገኝ አካባቢያቸውን በማስዋብ የድርሻቸውን ኃላፊነት እየተወጡ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

የሚሰሩት የከተማ ልማቶች ወጪ ቆጣቢና ከብክነት የፀዱ እንዲሆኑ የመሠረተ ልማት አቅራቢ ተቋማት የተቀናጀ እና የተናበበ ስራ መስራት እንዳለባቸውም ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026

በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል

ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...

Sep 7, 2026

በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...

Aug 31, 2026