የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

በአዲስ አበባ ከተማ የተመዘገቡ የልማት ስኬቶች የኢትዮጵያን የዕድገት ጉዞ የሚያሳልጡ ናቸው

Dec 8, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ህዳር 27/2018(ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ ከተማ የተመዘገቡ የልማት ስኬቶች የኢትዮጵያን የዕድገት ጉዞ የሚያሳልጡ መሆናቸውን በአዲስ አበባ ከተማ ህዝባዊ ውይይት መድረክ ተሳታፊዎች ተናገሩ።

''የጉባ ብስራቶች፤ የመደመር መንግሥት ትሩፋቶች" በሚል መሪ ሀሳብ በሀገር ሁለንተናዊ ለውጥና ቀጣይ ተስፋዎች የጋራ መፍትሔን ማምጣት ያለመ ህዝባዊ ውይይት በመዲናዋ ሁሉም ክፍለ ከተሞች ተካሂዷል፡፡


በአዲስ አበባ ህዝባዊ መድረክ ከተካሄደባቸው ክፍለ ከተሞች ውስጥም የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አንዱ ነው፡፡

በውይይቱም የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተዋል።

ባለፋት ዓመታት መንግስት የህዝብን የልብ ትርታ ለማድመጥ እስከታች ድረስ በመውረድ ሰላምን በማፅናት ልማትን በማፋጠን ስኬት መመዝገቡን ገልጸዋል።

የመልካም አስተዳደርን በማስፈን ረገድ ለውጦች ታይተዋል ያሉት የውይይቱ ተሳታፊዎች በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሕጋዊ የንግድ ስርዓትን ለመዘርጋት የተሄደበት ርቀትም ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል ብለዋል።

መንግስት ከህዝብ ጋር በመቀራረብ የኢትዮጵያን ብልፅግና በዘላቂነት ለማረጋገጥ የሚያከናውናቸው ተግባራትን አስተያየት ሰጪዎቹ አድንቀዋል።

በመንገድ መሰረተ ልማት ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችንም አፋጣኝ ምላሽ መስጠት እንደሚያስፈልግ ጠይቀዋል።

በተጨማሪም በመድረኩ ከጎርፍና ከደረቅ ጭነት ተሽካሪካሪ ማቆሚያ ስፍራ ጋር ተያይዞ በክፍለ ከተማው አሉ ያሏቸውን ጉዳዮች አንስተዋል፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ የፐብሊክ ሰሪቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ጀማሉ ጀምበር (ዶ/ር) የህዝብ ጥያቄዎች ለመፍታት ከተማ አስተዳደሩ በትጋት እየሰራ እንደሚገኝ በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ ገልጸዋል።

ዶክተር ጀማሉ ጀምበር አክለውም በመርካቶ የተጀመረው ህጋዊ የንግድ ስርአትን የመዘርጋት ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

የብልፅግና ፓርቲ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ በበኩላቸው የኢትዮጵያን ዘላቂ ብልፅግና ለማረጋገጥ ህዝብና መንግስት በጋራ ሊሰሩባቸው ይገባል ያሏቸውን ሃሳቦች አብራርተዋል።

አሁን ያለው ትውልድ የሀገርን ብልጽግና ለማረጋገጥ መንግስት እያከናወነ ያለውን ሁሉን አቀፍ ተግባራት ይበልጥ ስኬታማ ለማድረግ ሁሉም የድርሻውን አጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026

በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል

ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...

Sep 7, 2026

በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...

Aug 31, 2026