የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

ኢትዮጵያ ለግብርናው ዘርፍ በሰጠችው ልዩ ትኩረት በከፍተኛ ደረጃ ስኬት በማስመዝገብ ላይ ትገኛለች

Dec 8, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 28/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ ለግብርናው ዘርፍ በሰጠችው ልዩ ትኩረት በከፍተኛ ደረጃ የምርታማነት ስኬት በማስመዝገብ ላይ ትገኛለች ሲል መቀመጫውን ሳውዲ አረቢያ ያደረገው አሻርቅ ኒውስ ዘግቧል።

ኢትዮጵያ ከውጭ ሀገራት የስንዴ ዕርዳታ መቀበል ማቆሟን በይፋ ካወጀች በኋላ በስንዴ ምርት ሙሉ ለሙሉ ራሷን መቻሏል አትቷል።


ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቁጥር አንድ የስንዴ አምራች በመሆን ታሪክ ሰርታለች ያለው ሚዲያው፥ መንግሥት የተከተለው የግብርና ፖሊሲ የስንዴ ምርትን በዕጥፍ ለማሳደጉ አንዱ ምክንያት መሆኑን አንስቷል።

በተጨማሪም፥ ኢትዮጵያ በስንዴ ምርታማነት ላስመዘገበችው ትልቅ ስኬት ሶስት ምክንያቶችን አስፍሯል፥ እነሱም፦ከፍተኛ የመስኖ እርሻ መስፋፋት፣የተሻሻሉ ምርጥ ዘሮችንና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀሙእንዲሁም መንግሥት የምግብ ምርትን የሚደግፍ ፖሊሲ መተግበሩ ይህን አስገራሚ ለውጥ እንዲያመጣ አስችሎታል ብሏል።


ኢትዮጵያ ካላት 112 ሚሊየን ሔክታር መሬት ውስጥ 38 ሚሊዮን ሔክታር የሚጠጋው ለግብርና ምቹ መሆኑንም ገልጿል።

ሀገሪቱ በአንድ የግብርና ወቅት ብቻ 100 ሚሊዮን ቶን የሚደርስ ስንዴ የማምረት አቅም እንዳላት ነው አሻርቅ በትንታኔው የገለጸው።


የሀገሪቱ ዓመታዊ የስንዴ ፍጆታ ከ8 ሚሊየን ቶን የሚበልጥ ባለመሆኑ የሚተርፈውን ስንዴ ወደ ውጭ ሀገራት በመላክ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ማግኘት እንደምትችል አክሏል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026

በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል

ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...

Sep 7, 2026

በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...

Aug 31, 2026