የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

በመንግስት እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ተግባራት የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጡ ነው

Dec 8, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

‎ባሕርዳር ፤ ሕዳር 28/2018 (ኢዜአ) ፡- በመደመር መንግስት እይታ በተለያዩ ዘርፎች እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ተግባራት ሀገራዊ ዕድገቱን ከማፋጠን ባለፈ የሕብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እያረጋገጡ መሆናቸውን በአማራ ክልል የሰሜን ጎጃም ዞን እና የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።

መንግስት የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ይበይናሉ ተብሎ ትኩረት ከሰጣቸው ዋና ዋና የልማት ዘርፎች ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ የከተማና መሰረተ ልማት፣ ማዕድንና ቱሪዝም ይጠቀሳሉ።

የሰሜን ጎጃም ዞን የጎንጂቆለላ ወረዳ ነዋሪዎች ውስጥ አቶ አዳነ አለምኔ፤ የመደመር መንግስት በግብርናው ዘርፍ ሰፋፊና ውጤታማ የልማት ተግባራት እንዲከናወኑ እያስቻለ ይገኛል ብለዋል።


‎‎በተለይ በገጠር ኮሪደር ልማት በግብርናው ዘርፍ በሰብል ልማት፣ በአትክልትና ፍራፍሬ፣ በእንስሳት እርባታ፣ በተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ፣ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ትኩረት ተደርጎ በመስራቱ አበረታች ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እንዲመጣ እያገዘ መሆኑን ገልጸዋል።

‎‎ሜካናይዜሽንን በማስፋፋት ኋላቀር የሆነውን የግብርና አሰራር በመቀየር በግብርናው ዘርፍ መዋቅራዊ ለውጥ እንዲመጣ ማስቻሉም አንስተዋል።

‎‎በከተማ ልማት ዘርፍ ደግሞ ከተሞችን ፅዱና ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ እየተደረገ ያለው ጥረት ሕብረተሰቡን ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል።

‎‎በቀጣይም ሰላምን አፅንቶ ከማዝለቅ ጎን ለጎን እየተመዘገበ ያለውን ሁለንተናዊ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት አጠናክሮ ለማስቀጠል የተጀመሩ የልማት ተግባራት ከዳር እንዲደርሱ ሁላችንም የድርሻችንን ለማበርከት መረባረብ አለብን ብለዋል።

የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ ወለላ የኔው እንደገለጹት፤ የመደመር መንግስት መርሆዎች ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ዕድገትና ብልፅግና ፋይዳቸው የጎላ ነው።


‎በዚሕም በከተሞች እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎች ከተሞች ፅዱ፣ ሳቢና ማራኪ እንዲሆኑ ከማድረግ ባለፈ ዋነኛ የቱሪዝም መዳረሻ እንዲሆኑ እያስቻለ መሆኑን አንስተዋል።

‎‎በተለይ በባሕርዳር ከተማ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎች ባሕርዳር መርጠው የሚጎበኟት የቱሪዝም መዳረሻ ከተማ እንድትሆን ማስቻሉን ገልጸዋል።

‎በቀጣይም በተተኳሪ የልማት መስኮች የተጀመረው የልማት ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከመንግስት ጎን በመሆን የድርሻቸውን ለማበርከት ዝግጁ እንደሆኑም አረጋግጠዋል።

‎‎‎በመደመር መንግስት እይታ በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በማዕድን፣ በቱሪዝምና በከተማ መሰረተ ልማት ዘርፎች እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ተግባራትን መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እያከናወነ እንደሚገኝ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026

በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል

ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...

Sep 7, 2026

በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...

Aug 31, 2026