🔇Unmute
አዳማ፤ ታህሳስ 2 / 2018 (ኢዜአ)፡-በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን የሚገኙ ማእድናትን ሀብት በጥናት በመለየት ኢኮኖሚያዊ ፋይዳቸውን ለማሳደግ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የዞኑ ማእድን ልማት ፅህፈት ቤት ገለፀ።
የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ታደሰ ካሳዬ ለኢዜአ እንደገለጹት ዞኑ ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የማእድን ልየታ ጥናት እየሰራ ነው።
በዚህም ለኢንዱስትሪ ግብአትና ለግንባታ የሚያገለግሉ 17 ዓይነት ማእድናት እንደሚገኙ በጥናት መለየታቸውን ገልጸዋል።
በጥናት የተለዩት ማእድናትም ለኢንዱስትሪ ግብዓት የሚያገለግሉ ካዮሊን፣ ፑሚስ ፣ ሶዳ አሽ፣ ቢንቶናይት፣ ላይምስቶን የተሰኙ መሆናቸውን አብራርተዋል።
የማእድን ሀብቶቹን በማልማት ለስኳር፣ ለሲሚንቶ፣ ለሴራሚክስ ፋብሪካዎች እንዲውሉ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል።
እነዚህን ማዕድናትን አልምቶ ኢኮኖሚያዊ ጥቅማቸውን ለማሳደግ ባለፉት ዓመታት በማእድን ልማት ዘርፍ ለተሰማሩ 10 አነስተኛ እና መካከለኛ ደረጃ አልሚዎች ፈቃድ መሰጠቱን ጠቁመዋል።
የማእድን ልማቱን ውጤታማ ለማድረግ በዘርፉ ለተሰማሩ አልሚዎች የብድርና ሌሎችም ድጋፎች መመቻቸቱን አስታውቀዋል።
የማእድን ልማቱ ከአካባቢ ሥነ ምህዳር ጥበቃ ጋር በተናበበ መልኩ በማስኬድ በቁፋሮው የተጎዳ መሬትን መልሶ የማልማት ስራም ጎን ለጎን እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።
በአዳማ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የጂኦሎጂ ዲፓርትመንት ፔትሮሎጂስትና ጂኦ ኬሚስትሪ መምህርና ተመራማሪ (ዶ/ር) መለሰ አለማየሁ፣ የማዕድን ሀብት ለኢንዱስትሪ፣ ለግብርና፣ ለመሠረተ ልማት ግንባታ ግብአት በማዋል የውጭ ምንዛሬን ማሳደግ፣ ለተኪ ምርቶች ለማዋል ተጨማሪ አቅም እንደሚሆን ጠቁመዋል።
ዩኒቨርሰቲው በተለይም በዞኑ የሚገኝ የማዕድን ሀብትን በጥናትና ምርምር በመለየት ለድህነት ቅነሳ እና ለሥራ ዕድል ፈጠራ እንዲውሉ ድርሻውን እየተወጣ ነው ብለዋል።
ከአዳማ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር ማዕድናትን በማጥናት የጂኦሎጂ፣ ጂኦኬሚስትሪ፣ ጂኦፊዚካል እና የጂኦቴክኒካል ካርታ ሥራ ማከናወንና መረጃ ማሰባሰብ መካሄዱን አመላክተዋል።
በጥናቱ ለኮንስትራክሽን፣ ለሲሚንቶ እና ለኮስሞቲክስ ኢንዱስትሪ ግብዓት የሚያገለግሉ ማእድናት ክምችት በስፋት እንዳለ መረጋገጡን አስታውቀዋል።
ባህር ዳር፤ ሰኔ 2/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል የማዕድን ሀብት ልማት ዘርፉ በጥናትና ምርምር በመታገዙ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል እየፈጠረና ከፍተኛ የገቢ...
Jun 10, 2026
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 1/2018 (ኢዜአ)፦ ህዝባችን ለአገልግሎት ፍለጋ ጊዜና ገንዘቡን ሳያባክን ሃብቱን ለልማት እንዲያውል የምናደርገውን ጥረት አጠናክረን እንቀጥ...
Jun 9, 2026
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 19/2018 (ኢዜአ)፦ የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ መመረቅ ፍትሐዊና ሚዛናዊ የመሠረተ ልማት ዝርጋታን የሚያረጋግጥ መሆኑን ጠቅላ...
May 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/2018 (ኢዜአ)፡- ቱሪዝም የኢኮኖሚያችን አንዱ ምሰሶ እንደመሆኑ የሀገራዊ ዕድገታችንን የወደፊት አቅጣጫ እየቀረጸ ያለ ዘርፍ መሆኑ...
Apr 20, 2026