🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 30/2018(ኢዜአ)፦ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ቀልጣፋ የጉምሩክ አገልግሎትን ለማጠናከር ትልቅ ዕድል ይዞ መምጣቱን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ።
ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በስኬት መጠናቀቁን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን በይፋ ማስጀመራቸው ይታወቃል።
ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ተደራሽነትን ማስፋት፣ ለዜጎች እኩል ዕድል መፍጠር እንዲሁም በዜጎችና በተቋማት መካከል መተማመንን ማጎልበት ዋነኛ ዓላማዎቹ ናቸው።
የጉምሩክ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሙሉ ወርቅ ደረሰ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ ኮሚሽኑ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ትግበራ ወቅት የንግድ እንቅስቃሴን የሚያሳልጡ፣ ኮንትሮባንድን ለመቆጣጠር የሚያስችሉና በአጠቃላይ የኮሚሽኑን ስራዎች የሚያሻሽሉ ቴክኖሎጂዎች ወደ ሥራ አስገብቷል።
ቴክኖሎጂዎቹ ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችን ክትትል ለማጠናከር፣ የሰው ንክኪና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል እንዲሁም ደንበኞች ባሉበት ሆነው አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችሉ ናቸው ብለዋል።
በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የሚተገበረው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ደግሞ በጉምሩክ ዘርፍ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማዘመን እና ለማቀላጠፍ ትልቅ እድል ይዞ መምጣቱን ጠቅሰዋል።
ስትራቴጂውን ስኬታማ ለማድረግ የተቋማት ቅንጅት እንደ ዋነኛ የድጋፍ ማዕቀፍ መሆኑን በማንሳት፥ ኮሚሽኑ የበከሉን ይወጣል ብለዋል።
በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘ አሰራር ተግባራዊ መደረጉን ገልጸው፤ በሂደት ላይም ያሉ ቴክኖሎጂዎች በቀጣይ ወደ ስራ ይገባሉ ብለዋል።
ምክትል ኮሚሽነሯ እንደገለጹት በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የጉምሩክ አገልግሎትን በቴክኖሎጂ የተደገፈ የማድረግ ሰራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ።
ባህር ዳር፤ ሰኔ 2/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል የማዕድን ሀብት ልማት ዘርፉ በጥናትና ምርምር በመታገዙ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል እየፈጠረና ከፍተኛ የገቢ...
Jun 10, 2026
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 1/2018 (ኢዜአ)፦ ህዝባችን ለአገልግሎት ፍለጋ ጊዜና ገንዘቡን ሳያባክን ሃብቱን ለልማት እንዲያውል የምናደርገውን ጥረት አጠናክረን እንቀጥ...
Jun 9, 2026
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 19/2018 (ኢዜአ)፦ የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ መመረቅ ፍትሐዊና ሚዛናዊ የመሠረተ ልማት ዝርጋታን የሚያረጋግጥ መሆኑን ጠቅላ...
May 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/2018 (ኢዜአ)፡- ቱሪዝም የኢኮኖሚያችን አንዱ ምሰሶ እንደመሆኑ የሀገራዊ ዕድገታችንን የወደፊት አቅጣጫ እየቀረጸ ያለ ዘርፍ መሆኑ...
Apr 20, 2026