የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

በወራቤ ከተማ ከዘጠኝ ሄክታር መሬት በላይ የሚሸፍን የወንዝ ዳርቻ የኮሪደር የልማት ሥራ እየተፋጠነ ነው

Jan 9, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ወራቤ፤ ታኅሣስ 30/2018(ኢዜአ)፦ በወራቤ ከተማ ከዘጠኝ ሄክታር መሬት በላይ የሚሸፍን የወንዝ ዳርቻ የኮሪደር ልማት ሥራ እየተፋጠነ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ያሲን ከሊል ገለጹ፡፡

ከንቲባው ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ከተማዋን ውብ፣ ፅዱ እንዲሁም ለኑሮ እና ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት በልዩ ትኩረት እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡


ከዚህም ውስጥ አንዱ የወንዝ ዳርቻ ልማት መሆኑን ጠቅሰው በከተማ አስተዳደሩና በህብረተሰቡ ተሳትፎ ከ9 ሄክታር በላይ የሚሸፍን የወንዝ ዳርቻ ልማት ግንባታ እየተፋጠነ መሆኑን ተናግረዋል።


የወንዝ ዳርቻ የኮሪደር ልማት ሥራው የከተማውን ገፅታ ከመቀየር ባለፈ ምቹ የመኖሪያ አካባቢ እየፈጠረ መሆኑን ጠቅሰው የልማት ስራውን በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ውስጥ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ከልማት ሥራው በተጨማሪ የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ ካፍቴሪያ፣ የቅርጫትና የመረብ ኳስ መጫወቻ ሜዳ ፋውንቴን እንዲሁም ሰው ሰራሽ አነስተኛ ሐይቅ ማካተቱን ጠቅሰው የእነዚህ ግንባታዎች ስራም እየተጠናቀቀ መሆኑን ጠቁመዋል።

ከ2 ሺህ 500 በላይ ሰዎችን መያዝ የሚችል ቲያትር አዳራሽ፣ የእግር ኳስ ሜዳና ሌሎች የግንባታ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡


ከከተማዋ ነዋሪዎች መካከል ወጣት አብዲ ዋሴ እና አቶ ሸርፈዲን ሹሜ፤ የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራው የወራቤ ከተማን ለነዋሪው ምቹ እንድትሆን ከማድረግ በተጨማሪ ከሌሎች አቻ ከተሞች ጋር ተወዳዳሪ እንደሚያደርጋት ተናግረዋል።

በተለይም በከተማዋ የወንዝ ዳርቻን ለማልማት የተጀመረው ሥራ አካባቢው ቀድሞ የነበረውን መጥፎ ገጽታ በመቀየር ለመዝናኛና ለሥራ ዕድል እንዲውል መደረጉን ገልጸዋል።


በከተማዋ እየታየ ያለው ለውጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እያደረግን ያለውን ድጋፍ አጠናክረን እንቀጥላለን ነው ያሉት ነዋሪዎቹ።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026

በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል

ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...

Sep 7, 2026

በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...

Aug 31, 2026