🔇Unmute
ሰመራ፤ ጥር 6/2018(ኢዜአ)፦ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የሴቶችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሳደግ እንደሚያግዝ የአፋር ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ፋጡማ መሐመድ ተናገሩ።
"ፋይዳ ለሴቶች" በሚል መሪ ሐሳብ በአፋር ክልል የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል።

በመድረኩ የተገኙት የአፋር ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ፋጡማ መሐመድ እንዳሉት፤ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማሳደግ ያለው ሚና ከፍተኛ ነው።
በተለይም ሴቶች በፋይናንሱ ዘርፍ እና በዲጂታል የአገልግሎት አሰጣጥ የሚኖራቸው ተሳትፎ እንዲያድግና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።
ንቅናቄውን ተከትሎ እንደ አፋር ክልል በተያዘው ዓመት አንድ ሚሊዮን ሴቶች ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እንዲኖራቸው እየተሰራ ነው ብለዋል።

የንቅናቄ ስራው በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች እስከታች ድረስ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው፤ በዚህ ረገድ ለተያዘው ዕቅድ ስኬታማነት የሀገር ሸማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር ፅህፈት ቤት ኀላፊ አቶ አሚን መሐመድ በበኩላቸው እንደተናገሩት፤ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ በተለይም የሴቶችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው።

የዲጂታል መታወቂያ አገልግሎቱን በተቀላጠፈ ሁኔታ ተደራሽ ለማድረግ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑንም አመልክተዋል።
ሴቶች ተደራጅተው የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማግኘትም ሆነ በተለያዩ ሥራዎች ውስጥ በመሳተፍ ተጠቃሚ ለመሆን ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ያለው አበርክቶ ላቅ ያለ መሆኑንም አስረድተዋል።
የተጀመረውን የንቅናቄ ተግባሩ እንዲጠናከር በማድረግ በክልል ደረጃ የተያዘው ዕቅድ እንዲሳካ በቁርጠኝነት ይሰራል ብለዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ ከሰመራ ሎጊያ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች፣ ከተለያዩ ማህበራት፣ ከሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤትና ከሰመራ ዩኒቨርሲቲ የመጡ ሴቶች ተገኝተው ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያውን ለማግኘት ተመዝግበዋል።
ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...
Sep 11, 2026
ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...
Sep 10, 2026
ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...
Sep 7, 2026
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...
Aug 31, 2026