የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

የኢጋድ የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ተሳትፎ እና ቀጣናዊ የትኩረት መስኮች

Feb 13, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ የካቲት 2/2018(ኢዜአ)፦ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) በ39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ሰላም እና የውሃ ሀብቶችን ጨምሮ ቀጣናዊ የትኩረት መስኮች ላይ ትኩረት ያደረገ ተሳትፎ እንደሚኖረው አስታወቀ።

የህብረቱ ጉባኤ የካቲት 7 እና 8 ቀን 2018 ዓ.ም “ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በመል መሪ ሐሳብ በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ይካሄዳል።

ቀደም ብሎ የካቲት 4 እና 5 ቀን 2018 ዓ.ም 48ኛው የህብረቱ የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ይካሄዳል።

በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን(ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ የተመራ ልዑክ በጉባኤው ላይ ይሳተፋል።

ኢጋድ በቀጣናው ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ይዞ እንደሚቀርብ አስታውቋል።

ሰላም እና ደህንነት፣ የአየር ንብረት፣ የውሃ ሀብቶች እና ቀጣናዊ ትስስር ከአጀንዳዎቹ መካከል በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው።

ኢጋድ በጉባኤው የሚኖረው ተሳትፎ ከቀጣናዊ አጀንዳዎች እና ከአጀንዳ 2063 ግቦች ጋር የተቆራኙ መሆናቸውን አመልክቷል።

በዋና ጸሀፊው የሚመራው ልዑክ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን፣ ከህብረቱ አባል ሀገራት ጋር በተለያዩ ቀጣናዊ እና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክር ተመላክቷል።

ኢጋድ የቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች የቅንጅት እና የትብብር ማዕቀፍ ሊቀ መንበርነት በጉባኤው ላይ ለደቡባዊ አፍሪካ ልማት ትብብር ኮንፈረንስ(ሳዴክ) ያስረክባል።

ይህም ለአህጉራዊ ትብብር ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ ገልጿል።

በሚኖሩት ምክክሮች እና ውይይቶች ኢጋድ የአፍሪካ ቀንድ የትኩረት መስኮችን ወደ አህጉራዊው መድረክ በማምጣት የሰላም፣ አይበገሬነትና የጋራ ብልጽግና አጀንዳዎች ለማሳለጥ እንደሚሰራ መግለጹን ኢዜአ ከተቋሙ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026

በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል

ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...

Sep 7, 2026

በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...

Aug 31, 2026