የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

ዩኒቨርሲቲው የኢንዱስትሪ ምርታማነትን የሚያሳድጉ ብቁ ባለሙያዎችን እያፈራ ነው

Feb 13, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤የካቲት 2/2018 (ኢዜአ)፡-የኢንዱስትሪውን ዘርፍ ምርታማነት የሚያሳድጉ ብቁ ባለሙያዎችን በማፍራት ረገድ ከፍተኛ ድርሻ እየተወጣ መሆኑን አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ።

አስረኛው ዓለም አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ "ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ለኢንዱስትሪ" በሚል መሪ ሀሳብ መካሄድ ጀምሯል።


የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ደረጃ እንግዳ (ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለጹት፤ ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ ኮንፈረንስ ላይ ከ96 በላይ የምርምር ሥራዎች ለውይይት የሚቀርቡ ሲሆን የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ትልቅ ዕድል የሚፈጥር ነው፡።

ዩኒቨርሲቲው ትኩረቱን በምርምር እና በተግባር ተኮር ትምህርት ላይ ማድረጉን የጠቀሱት ፕሬዝዳንቱ፣ ይህም ተማሪዎች የኢንዱስትሪውን ችግር በቀጥታ መፍታት የሚችሉ የፈጠራ ሥራዎችን ይዘው እንዲወጡ እያገዘ መሆኑን ገልጸዋል።

ተማሪዎች ከንድፈ-ሀሳብ ባለፈ በዘመናዊ ላቦራቶሪዎች እንዲሰለጥኑ በመደረጉ፣ ለሥራ ዝግጁ የሆኑ ባለሙያዎች እየበቁ እንደሚገኙም አክለዋል።

በተጨማሪም በዩኒቨርሲቲው የሚወጡ የፈጠራ ውጤቶች ወደ ኢንዱስትሪው እንዲሸጋገሩ በማድረግ የምርት ሂደቱን ለማዘመን ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው ከተለያዩ ፋብሪካዎችና የቴክኖሎጂ ተቋማት ጋር በቅንጅት በመስራት የተማሪዎችን የተግባር ልምምድ ውጤታማ እያደረገ መሆኑንም አስረድተዋል።

በቀጣይም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ የፈጠራ ሥራዎችን ለማፍለቅና የኢንዱስትሪ-ዩኒቨርሲቲ ትስስሩን ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።


የኢትዮጵያ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሚልኬሳ ጃጋማ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በአዋጅ የተደገፈ የዩኒቨርሲቲ-ኢንዱስትሪ ትስስር በመፈጠሩ የኢንዱስትሪ ችግሮችን የሚያጠናና መፍትሄ የሚሰጥ የሰው ኃይል እየቀረበ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህ ረገድም የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እያከናወነ ያለው ተግባር አመርቂ መሆኑን ጠቁመዋል።

የቤልጂየሙ ትራይዲል ሃውስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ማይክል ሎትስ (ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያ በኢንዱስትሪው ዘርፍ ያስመዘገበቻቸው ለውጦች የሚታዩና የሚዳሰሱ መሆናቸውን ገልጸው ለዚህም ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 እና የአምስት ሚሊዮን ኮደሮች ኢኒሼቲቭ ትልቅ ማሳያዎች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።


በአሁኑ ወቅት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በኢንዱስትሪ፣ በቤቶች ልማትና በሌሎች ዘርፎች በቅርበት እየሰሩ መሆኑን ጠቁመው፤ በቀጣይም ይህ ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026

በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል

ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...

Sep 7, 2026

በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...

Aug 31, 2026