🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ የካቲት 23/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት ሂደት የኢንዱስትሪው ዘርፍ ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገበ መምጣቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ገለጹ።
የብሔራዊ የአምራች ኢንዱስትሪ ካውንስል በኦሮሚያ ክልል ሸገር፣ ቢሾፍቱ እና አዳማ ከተሞች የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ትናንት እና ዛሬ የመስክ ምልከታ አድርጓል።

ምልከታው የሀገሪቱን የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ አቅም ለመገምገም እና በዘርፉ የሚታዩ ማነቆዎችን ለመለየት ያለመ ነው።
የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል በጉብኝቱ ማጠናቀቂያ ላይ እንደገለጹት፤ በሦስቱ ከተሞች የታዩት እንቅስቃሴዎች ኢትዮጵያ በዘርፉ የጀመረችው ጉዞ ተስፋ ሰጪ መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው።
በጉብኝቱ ወቅት ገቢ ምርቶችን በመተካት፣ የወጪ ምርትን በመጨመር እና ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ትልልቅ አቅም ያላቸው ኢንዱስትሪዎች መኖራቸውን ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል።
በተለይም የብረታ ብረት፣ የኮንስትራክሽን ሴራሚክ ምርቶች፣ የፋርማሲዩቲካል ምርቶች፣ የምግብ እና ምግብ ነክ ኢንዱስትሪዎች የሚታየው እንቅስቃሴ የሚበረታታ መሆኑ ጠቅሰዋል።
ካውንስሉ ከተቋቋመባቸው ዋና ዓላማዎች አንዱ የመንግስት ድጋፍ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ መገምገም እንደሆነ የጠቀሱት ሚኒስትሩ፤ በየደረጃው ያለው የመንግስት መዋቅር አምራቾችን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን በተግባር ማየታቸውን ገልጸዋል።

መሬት በማቅረብ፣ መሠረተ ልማት በማሟላት እና የግብዓት ችግሮችን በመፍታት ረገድ የተሰሩ ሥራዎች ለአምራቾች ትልቅ የመተማመን መንፈስ የሚፈጥሩ ናቸው ብለዋል።
ኢንዱስትሪዎች አሁን ካሉበት አቅም በላይ እንዲያድጉ እና የማምረት አቅማቸው እንዲጨምር የተለያዩ ተግባራት እንደሚቀሩ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
በክልሉ የታዩት አዳዲስ ፕሮጀክቶች እና ነባር ፋብሪካዎች ኢትዮጵያ በኢንዱስትሪ ላይ የተመሰረተ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት የያዘችውን ራዕይ እውን ለማድረግ የሚያስችሉ መሆናቸውን ካውንስሉ አረጋግጧል ብለዋል።
ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...
Sep 11, 2026
ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...
Sep 10, 2026
ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...
Sep 7, 2026
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...
Aug 31, 2026