የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

ንቅናቄው የአምራች ኢንዱስትሪ ማነቆዎችን በመፍታት ቁልፍ ሚና እየተጫወተ ነው

Mar 4, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ የካቲት 24/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በዘርፉ የነበሩ ተግዳሮቶችን በመቅረፍ በኩል ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑን ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉ የተለያዩ አምራቾች ገለጹ።

የብሔራዊ የአምራች ኢንዱስትሪ ካውንስል በኦሮሚያ ክልል ሸገር፣ ቢሾፍቱ እና አዳማ ከተሞች የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎችን የመስክ ምልከታ አድርጓል።


ምልከታው የሀገሪቱን የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ አቅም ለመገምገምና በዘርፉ የሚታዩ ማነቆዎችን ለመለየት ያለመ ነው።

በዚሁ ጊዜ ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት አምራች ኢንዱስትሪዎች የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የአምራች ኢንዱስትሪው ማነቆዎች በመፍታት ቁልፍ ሚና እየተጫወተ እንዳለ ተናግረዋል።

የኬብሮን ኢንዱስትሪ ባለቤት ዮሴፍ ታደሰ እንደገለጹት፤ ድርጅታቸው ላለፉት 25 ዓመታት ለግንባታና ለተለያዩ ኢንዱስትሪዎች የሚውሉ የብረት ምርቶችን በተለይም የአርማታ ብረትና ቱቦላሬ በማምረትና በማቅረብ ላይ ይገኛል ብለዋል።

ባለፉት ጥቂት ዓመታት መንግስት ለዘርፉ የሰጠው ልዩ ትኩረት ድርጅታቸው በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ እንዲገባ ማድረጉን ጠቁመዋል።

በተለይም የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በዘርፉ የነበሩ ተግዳሮቶችን በመቅረፍ አዲስ መነቃቃት መፍጠሩን ተናግረዋል።


የአንታ ማኑፋክቸሪንግ ባለቤት አንተነህ ታደሰ በበኩላቸው ተቋሙ ላለፉት 30 ዓመታት በመካከለኛና በከባድ ተሽከርካሪዎች አካል ግንባታ(Vehicle Body Building) ላይ በመሰማራት ለሀገሪቱ የትራንስፖርት ዘርፍ እድገት የላቀ ሚና ሲጫወት ቆይቷል ነው ያሉት።

በአሁኑ ወቅትም በቴክኖሎጂ የታገዘ ዘመናዊ አሰራርን በመከተል የውጭ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለሰላሳ ዓመታት በጽናት ለቆዩ ድርጅቶች አዲስ አቅም እየፈጠረ እና የቆዩ ማነቆዎችን እየቀረፈ ይገኛል ብለዋል።


የረጲ ሳሙናና ዲተረጀንት ፋብሪካ የዋና ሥራ አስኪያጅ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ብርሃኑ ለማ በበኩላቸው፤ ፋብሪካው የፅዳት መጠበቂያ ምርቶች ምርት ላይ መሰማራቱንና ፋብሪካው በአሁኑ ወቅት ዊልማር ኢንተርናሽናል ከተሰኘ ታዋቂ ዓለም አቀፍ ኩባንያ ጋር በመተባበር ሥራውን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለፋብሪካው ምርት ጥራትና ብዛት ማደግ በዚህም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን የጀርባ አጥንት እንደሆነው ተናግረዋል።

በመንግስት እየተደረገ ያለው ድጋፍ ፋብሪካው አሁን ካለበት አቅም በላይ እንዲያመርት እያገዘው መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026

በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል

ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...

Sep 7, 2026

በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...

Aug 31, 2026