የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

የግብርናውን ዘርፍ እድገት ለማፋጠን አዳዲስ የምርምር ሥራዎች እየተካሄዱ ነው 

Mar 9, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አምቦ፤ የካቲት 28/2018 (ኢዜአ)፦ የግብርናውን ዘርፍ እድገት ለማፋጠን አዳዲስ የምርምር ሥራዎችን እያካሄደ መሆኑን የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ገለጸ።

በክልሉ በቆላማ አካባቢዎች የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን የመስኖ ልማት ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል

ኢንስቲትዩቱ በአምቦ ግብርና ምርምር ማዕከል የተሻሻሉ የወተት ላሞች ዝርያን ለሞዴል አርሶ አደሮች የማስተላለፍ እና የዕፅዋት ጥበቃ ምርምር ቤተ-ሙከራ ቁሳቁሶች የርክክብ ሥነ-ሥርዓት አካሂዷል።


የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ንጉሤ ደቻሳ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ኢንስቲትዩቱ የግብርናውን ዘርፍ ይበልጥ ለማዘመን የተለያዩ አዳዲስ የምርምር ሥራዎችን እያካሄደ ይገኛል።

የግብርናውን ዘርፍ በቴክኖሎጂ በማስደገፍ የምግብ ሉዓላዊነትን ከማረጋገጥ ባለፈ፣ የሀገሪቱን እድገት ማፋጠን የሚችሉ በሳይንሳዊ ምርምር የተደገፉ ዘርፈ-ብዙ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቅሰዋል።


ለአብነትም በባዮ-ቴክኖሎጂ ሥራዎች ላይ ትኩረት በመስጠት ምርትና ምርታማነት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር መደረጉን ገልጸዋል።

በቀጣይም የግብርናውን ዘርፍ እድገት ለማፋጠን የሚያግዙ አዳዲስ የምርምር ሥራዎች በተጠናከረ መልኩ የሚቀጥሉ መሆኑን አንስተዋል።

የአምቦ ግብርና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር ጃማል ቶላ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የምርምር ማዕከሉ የአካባቢውን ማህበረሰብ ችግር መፍታት የሚችሉ የተለያዩ የግብርና ምርምር ሥራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ጠቅሰዋል።


ከተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) ድጋፍ የተገኘ የዕፅዋት ጥበቃ ምርምር ቤተ-ሙከራ ቁሳቁሶችን ኢንስቲትዩቱ ለአምቦ ግብርና ምርምር ማዕከል ማስረከቡንም አስታውሰዋል።

የቤተ-ሙከራ ቁሳቁሶቹ የዕፅዋት በሽታዎችን ለመለየትና የአካባቢውን አርሶ አደሮች ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እንደሚረዱ ተናግረዋል።

ለብዙ ዓመታት የምርምርና ብዜት ሥራ ሲከናወንባቸው የነበሩ የተሻሻሉ የወተት ላሞች ለሞዴል አርሶ አደሮች ተላልፈው መሰጠታቸውን የተናገሩት ደግሞ በአምቦ ግብርና ምርምር ማዕከል የጊንጪ መለስተኛ ግብርና ማዕከል ዳይሬክተር ተስፋዬ አበራ (ዶ/ር) ናቸው።


ማዕከሉ የወተት ላሞቹን ካስተላለፈ በኋላም አርሶ አደሮቹን በአንድ መንደር በማደራጀት አስፈላጊውን ሙያዊ ድጋፍ በማድረግ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ እንደሚሠራም ገልጸዋል።

የአካባቢው አርሶ አደሮችም የተሻሻሉ የወተት ላሞች ዝርያ በማግኘታቸው መደሰታቸውን ገልጸው፤ ለላሞቹ አስፈላጊውን ጥበቃ በማድረግ ገቢያቸውን ለማሻሻልና በሀገራዊ እድገት ውስጥ ለመሳተፍ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።


የአምቦ ወረዳ ነዋሪው አርሶ አደር አቶ ወልደሰማያት ለታ፤ ከግብርና ሥራቸው ጎን ለጎን የወተት ላሞቹን በማርባት ከሚያገኙት ምርት የምግብ ዋስትናቸውን ከማረጋገጥ ባለፈ ገቢያቸውን ለማሳደግ እንደሚሠሩ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ቱሪዝም የሀገራዊ ዕድገታችንን የወደፊት አቅጣጫ እየቀረጸ ያለ ዘርፍ መሆኑን እያስመሰከረ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 

‎አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/2018 (ኢዜአ)፡- ቱሪዝም የኢኮኖሚያችን አንዱ ምሰሶ እንደመሆኑ የሀገራዊ ዕድገታችንን የወደፊት አቅጣጫ እየቀረጸ ያለ ዘርፍ መሆኑ...

Apr 20, 2026

የኮደርስ ስልጠና ቀልጣፋና ዘመናዊ የሕዝብ አገልግሎት መስጠት አስችሏል

ጅማ፤ ሚያዝያ 6/2018(ኢዜአ)፡- በጅማ የኮደርስ ስልጠና የወሰዱ የመንግሥት ሠራተኞች ቀልጣፋና ዘመናዊ የሕዝብ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ እያገዛቸው መሆኑን...

Apr 14, 2026

በምዕራብ ሸዋ ዞን የፍራፍሬ ልማትን የማስፋፋት ስራ በትኩረት እየተከናወነ ነው

አምቦ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን የፍራፍሬ ልማትን የማስፋፋት ስራ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር ገለጸ።...

Mar 27, 2026

ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የደረሰው የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሂደት

በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ ያቀረበችው እ.አ.አ 2003 ነበር። ኢትዮጵያ በወቅቱ ጥያቄውን ካቀረበች በ...

Mar 27, 2026