የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

ባለፉት ሰባት ዓመታት በፊስካል ፖሊሲና በመንግስት ፋይናንስ የተመዘገቡ ስኬቶች

Mar 11, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 1/2018(ኢዜአ)፦ ባለፉት ሰባት አመታት (ከ2010 - 2017 ዓ.ም) በፊስካል ፖሊሲና በመንግስት ፋይናንስ ረገድ ስኬቶች መመዝገባቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ እንዳመለከተው የመንግሥት የበጀት ጉድለትን ለመቀነስ በተወሰደው ርምጃ ከሀገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት -2 ነጥብ 5 በመቶ የነበረው የበጀት ጉድለት ወደ -0 ነጥብ 9 በመቶ ዝቅ ብሏል።

የመንግስትን ገቢ የሚያሻሽሉ ሪፎርሞች ተግባራዊ በመደረጋቸው ጠቅላላ ገቢው ከ5 እጥፍ በላይ አድጓል።


የመንግስት የወጪ አቅጣጫው ድህነትን ለመዋጋትና ልማትን ለማረጋገጥ እንዲውል በመደረጉም ድህነት ተኮር ወጪ ከ5 እጥፍ በላይ አድጓል።

የበጀት ተዓማኒነትን ለማረጋገጥ የሚያግዝ የመካከለኛ ዘመን የፊስካል ማዕቀፍ እንዲጠናከር በመደረጉ የበጀት አፈጻጸሙ ተሻሽሏል።

ከብሔራዊ ባንክ የሚወሰደው ቀጥታ ብድር እንዲቀር በመደረጉ የዋጋ ንረትን ለመግታት አስተዋጽኦ አድርጓል።

መንግሥት የተቀናጀ የፋይናንስ አስተዳደር የመረጃ ስርዓት መዘርጋቱን ገልጾ፤ የዲጂታል ክፍያ አማራጮችን በመተግበር የፋይናንስ ስርዓቶችን በማዘመን የፋይናንስ አስተዳደር ስርዓት ማዘመን እንደተቻለ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026

በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል

ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...

Sep 7, 2026

በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...

Aug 31, 2026