የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

የትምህርት ዘርፉን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለመደገፍ ከተቀመጡ ወሳኝ ጉዳዮች አንዱ ደህንነቱ የተጠበቀ የትምህርትና ምዘና ስርዓት መዘርጋት ነው-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

Mar 20, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 10/2018 (ኢዜአ)፡-በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የትምህርት ዘርፉን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለመደገፍ ከተቀመጡ ወሳኝ ጉዳዮች አንዱ ደህንነቱ የተጠበቀና በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ የትምህርትና ምዘና ስርዓት መዘርጋት ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ዛሬ ከክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ከከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች፣ ከትምህርት ዘርፍ አመራሮችና ከባለድርሻ አካላት ጋር የኢትዮጵያ ብሔራዊ የዲጂታል ፈተና ምዘና ስርዓት እና የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታን በተመለከተ በበይነ መረብ ውይይት አካሂደዋል።


በዚህም እንደ ሀገር የተቋቋመው የፈተና ብሔራዊ ግብረ ሀይል በቅደመ ዝግጅት ስራዎች ያከናወናቸው ስራዎች የደረሱበትን የስራ ሂደት ገምግመዋል።

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ሙሉ በሙሉ ወደ ኦንላይን ትግበራ ለማሸጋገርና ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒ የምዘና ስርዓት ለመገንባት ሁሉም ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል በለዋል።

በሁሉም ክልሎች እና በሁለት የከተማ አስተዳደሮች በተመሳሳይ ስታንዳርድ 1452 ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እስከ መጪው ነሀሴ ወር ተጠናቀው ወደ ስራ እንዲገቡ መግባባት ላይ ደርሰናል።

በተጨማሪም ለአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ለመማሪያ የሚያገለግሉ እና ታትመው የተሰራጩ መጽሀፍት ወደ ትምህርት ቤቶች እንዲሰራጩ እንዲሁም ከቅድመ አንደኛ እስከ ስድስተኛ ክፍል ድረስ የሚያገለግሉ መጽሀፍት እስከ መጪው መስከረም ድረስ ታትመው ወደ ትምህርት ቤቶች እንዲሰራጩ አቅጣጫ አስቀምጠና ነው ያሉት።

በመጨረሻም የዲጂታል ትምህርት ፈተና ምዘና ስርዓቱ ከሀገራዊ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን መርሆዎች ጋር መጣጣሙን በማረጋገጥ፤ የተጀመረውን ዝግጅት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ መግባባት ላይ መደረሱን ጠቁመዋል።

#Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026

በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል

ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...

Sep 7, 2026

በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...

Aug 31, 2026