🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 13/2018 (ኢዜአ)፦ የግብርናውን ክፍለ-ኢኮኖሚ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ለግብርና ሜካናይዜሽን ከፍተኛ ትኩረት መሰጠቱን የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ ገለጹ።
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር በርካታ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎችን እያበረከተ ነው
አቶ አዲሱ አረጋ በግብርና ሚኒስቴር የሜካናይዜሽን ልህቀት ማዕከል ከ2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የግብርና መሳሪያዎች ለክልል የግብርና ኃላፊዎችና ተወካዮች አስረክበዋል።

ሚኒስትሩ በርክክብ ስነ ስርዓቱ ወቅት እንዳሉት፣ የግብርና ትራንስፎርሜሽን የግብርና ስርዓቱን ወደ ሜካናይዜሽን በማሸጋገር ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድግ ነው።ይህም የግብርና ምርትን ከራስ አልፎ ለገበያ ማቅረብ የሚያስችል እንደሆነም አመላክተዋል።
ከዚህ በፊት በነበረው ግብርና መር ፖሊሲ የአርሶ አደሩ ህይወት ላይ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት አለመቻሉን አንስተዋል።
በተለይ አነስተኛ ይዞታ የነበራቸው አርሶ አደሮች የሜካናይዜሽን መሳሪያዎችን መግዛት የሚችሉበት እድል እንዳልነበረም አውስተዋል።

የመደመር መንግስት የግብርና መሳሪያዎች ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ በማድረግ ለአርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል።
የግብርና ትራንስፎርሜሽን ለመደመር መንግሥት ዋነኛ አጀንዳ መሆኑንም ተናግረዋል።
አርሶ እና አርብቶ አደሮችን የግብርና መሳሪያዎች ተጠቃሚ ማድረግ ትኩረት የተሰጠው መሆኑንም አመላክተዋል።
በዚህም ባለፉት የለውጥ ዓመታት በስርዓተ-ምግብና በምግብ ሉዓላዊነት ላይ ከፍተኛ እመርታዊ ለውጥ መምጣቱን ተናግረው፤ ይህም በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

ድጋፉን የተረከቡ የክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊዎች በበኩላቸው ድጋፉ የግብርና ዘርፉን በማዘመን ምርታማነትን የሚያሳድግ ነው ብለዋል።

የጋምቤላ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አንድሪው ቱት፤ ድጋፉ የግብርና ስራውን ወደ ሜካናይዜሽን የሚያሸጋግር ነው ብለዋል።
የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ባበክር ኸሊፋ በበኩላቸው፤ ድጋፉ በክልሉ እየተከናወኑ ላሉ የግብርና ስራዎች ውጤታማነት ትልቅ አቅም እንደሚሆን አመላክተዋል፡፡

ድጋፉ የክልሉን የግብርና ምርትና ምርታማነት የሚያሳድግ ነው ያሉት ደግሞ በሲዳማ ክልል የራሮ ሽበዲኖ ወረዳ የአርሶ አደሮች የግብርና ምርት ቢዝነስ ንግድ ካምባኒ የክላስተር ሰብሳቢ በየነ ያርሶ ናቸው።

የግብርና መሳሪያዎቹ 63 ትራክተሮች፣ 71 ወኪንግ ትራክተሮች፣ 150 የሩዝ ማቀነባበሪያ ማሽኖች፣ 78 ባለ ብዙ የእንቁላል መታቀፊያዎች እና የአንድ ደረጃ መፈልፈያዎች፣ 5 የከርሰ-ምድር ውሃ ማውጫ ማሽኖች፣ 460 በፀሐይ ሃይል የሚሰሩ የውሃ መሳቢያ ፓምፖች፣ 15 የመስክ መኪኖች፣ 243 ሞተር ሳይክሎች፣ 980 ዴስክ ቶፖችና ላፕቶፖች እንዲሁም 5 የቡና ላቦራቶሪዎች ናቸው።
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፦ የሲሚንቶ ንግድ እና መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በተመለከተ የወጡ መመሪያዎች ገበያውን በማረጋጋትና የዋጋ ግሽበትን በመቀ...
Feb 12, 2025