🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018(ኢዜአ)፦የጎንደር ዳግም ትንሳዔ፤ የታሪክ እና የዘመናዊነት ውህደት በኮሪደር ልማት
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በጎንደር ከተማ የገጠር ቀበሌዎች በገጠር ኮሪደር የተሰሩ ቤቶችን መርቀው ለተጠቃሚዎች አስተላልፈዋል፡፡
ጎንደር ከተማዋ ብቻ ሳይሆን ገጠሩም በኮሪደር ልማት አዲስ የታሪክና የሥልጣኔ ምዕራፍ ተከፍቶለታል
ጎንደር የኢትዮጵያ የልዕልና ምልክት፣ የሕብረ-ብሔራዊነት ማሳያና ጥንታዊነትን ከዘመናዊነት እንደሰምና ወርቅ ያስማማች ልዩ ከተማ ናት ብለዋል፡፡

በስነ ጥበብ፣ በስልጣኔ እና የዓለም ቅርስ በሆነው ፋሲል ግንብ የምትታወቀው ጥንታዊቷ ጎንደር ከተማ ዛሬ ላይ አዲስ ገጽታን ተላብሳ አምራና ተውባ ትገኛለች።
ለዘመናት ምቹ ባልነበሩ መንገዶችና ባረጁ መንደሮች ታጥራ የቆየችው ታሪካዊቷ ከተማ፤ በአሁኑ ወቅት በፈጣን የእድገት ግስጋሴ ላይ ትገኛለች፡፡
በተለይ ደግሞ የኮሪደር ልማት በከተማዋ መሰራት ከተጀመረ ወዲህ ታሪካዊቷ ከተማ ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ይበልጥ ለቱሪስቶች ሳቢ እንድትሆን አድርጓታል::
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በከተማ ደረጃ የተጀመረው የኮሪደር ልማት አድማሱን በማስፋት ወደ ገጠር መንደሮችና አጎራባች ቀበሌዎች መስፋፋቱ፣ በነዋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ደስታን ፈጥሯል።

የጎንደር ዳግም ትንሳዔ፤ የታሪክ እና የዘመናዊነት ውህደት በኮሪደር ልማት እውን እየሆነ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል፡፡
በጎንደር የገጠር ቀበሌ የተገነቡ የገጠር ኮሪደር አካባቢውን ወደ አዲስ የታሪክና የሥልጣኔ ምዕራፍ ያሸጋገረ ደማቅ አሻራ ነውም ብለዋል፡፡
የልማት ስራው መፋጠኑን ያስተዋሉት ነዋሪዎች የደስታ ስሜታቸውን በተለያዩ መንገዶች እየገለጹ ይገኛሉ፡፡

የሳይና ሳቢያ ቀበሌ ነዋሪና የገጠር ኮሪደር ልማት ተጠቃሚ አቶ ደሴ ሲሳይ በሰጡት አስተያየት፤ ከዚህ በፊት የገጠር የኮሪደር ልማት በአካባቢያቸው አልነበረም፡፡
አሁን ላይ በአካባቢያቸው እየተስፋፋ የሚገኘው አዲሱ የገጠር ኮሪደር ልማት የዳግም ልደት ያህል ትልቅ ትርጉም እንደሰጣቸው ተናግረው ትልቅ የደስታ ስሜት እንደፈጠረላቸውም ነው የገለጹት፡፡
አቶ ጌታ ደምሴ በበኩላቸው እንደተናገሩት፤ የገጠር ኮሪደር ልማት አካባቢያቸውን ከመቀየር ባለፈ የማህበረሰቡን የቤት ውስጥ አኗኗርና የጤና አጠባበቅ እየቀየረ ይገኛል።

በአንድ ጣራ ስር ከከብቶች ጋር አብሮ የመኖር ልማድን በመለየት ልማቱ ለገጠሩ ማህበረሰብ አዲስና ጽዱ የኑሮ ዘይቤን ይዞ በመምጣቱ መደሰታቸውን ነው የገለጹት፡፡
ሳሎን ቤት፣ መኝታና መታጠቢያ የተሟላለት ቤት ውስጥ መኖር በመጀመራቸው እጅግ ደስ መሰኘታቸውን የገለጹት ደግሞ አቶ ዮሐንስ ባዜ እና አንጓች ውባዬ ናቸው፡፡

መንግስት ከሚያወርዳቸው አቅጣጫዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቅሰው የገጠር ኮሪደሩ አኗኗራቸውን በተግባር የቀየረ በመሆኑ መደሰታቸውን ጠቁመዋል፡፡
ቤቶቹ ህብረተሰቡን በማስተባበር በአካባቢው ቁሳቁስ የተገነቡ ሲሆን ጤና ጣቢያን ጨምሮ ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን አካትተዋል፡፡
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፦ የሲሚንቶ ንግድ እና መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በተመለከተ የወጡ መመሪያዎች ገበያውን በማረጋጋትና የዋጋ ግሽበትን በመቀ...
Feb 12, 2025