የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

በዞኑ ከ52 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በበልግ ሰብል ተሸፍኗል

Apr 1, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ደሴ፤መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን ከ52 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በበልግ ሰብል መሸፈኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ፡፡

በደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ የሰብል ልማት ቡድን መሪ አቶ ይመር ሰይድ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በዞኑ የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ሉአላዊነትን ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው።

የበልግ ሰብል ልማቱን ለማሳካት የሜካናይዜሽንና የግብአት እቅርቦት በወቅቱ ለአርሶ አደሩ ተደራሽ መደረጉን አንስተዋል።

እየጣለ ያለውን የበልግ ዝናብ በመጠቀም ከ104 ሺህ 600 ሄክታር የሚበልጥ መሬት በማልማት ከ1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን ገልጸዋል።

እስካሁን በተደረገው ጥረትም ከ52 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች በዘር መሸፈን ጠቁመዋል።

የዘር ሥራውን አጠናክሮ በማስቀጠል እስከ ያዝነው ወር መጨረሻ እቅዱን ሙሉ በሙሉ ለማሳካት አመራሩና ባለሙያው የተጠናከረ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በዞኑ በኩታበር ወረዳ 03 ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር አህመድ ዳውድ ፤ እየጣለ ያለውን ዝናብ በመጠቀም አንድ ሄክታር የሚጠጋ ማሳቸውን በስንዴና ገብስ ዘር መሸፈናቸውን ተናግረዋል።

ዝናቡ ለሰብል ልማቱ ምቹ በመሆኑ በማሳቸው ላይ የአረምና ተባይን የመከላከል ስራዎችን በማከናወን ከ30 ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።

ሌላው የዚሁ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ሰይድ ከበደ በበኩላቸው፤ እየጣለ ያለውን የበልግ ዝናብ ተጠቅመው ያላቸውን ከግማሽ ሄክታር በላይ መሬት በስንዴ እና ገብስ ዘር መሸፈናቸውን ተናግረዋል።

የተሻሻሉ አሰራሮችንና ቴክኖሎጂን በመጠቀም በምግብ ራሴን ከመቻል ባለፈ ትርፍ ምርት በማምረት ለገበያ ለማቅረብ እየሰራሁ ነው ብለዋል።

በደቡብ ወሎ ዞን ባለፈው ዓመት በበልግ ከለማው 60 ሄክታር መሬት ከ360 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት መገኘቱን ከዞኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026

በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል

ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...

Sep 7, 2026

በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...

Aug 31, 2026