🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018(ኢዜአ)፦ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም በንግዱ ዘርፍ ተጨባጭ ለውጥ እንዲመዘገብ ማስቻሉን የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሣሁን ጎፌ(ዶ/ር) ገለጹ።
በአፋር ክልል የተገነባውን የሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል በዛሬው ዕለት ሚኒስትር ካሣሁን ጎፌ(ዶ/ር) እና የአፋር ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አወል አርባ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
በምረቃ መርሃ ገብሩ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሣሁን ጎፌ(ዶ/ር)፣ መንግሥት የቀየሰው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም በንግዱ ዘርፍ ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ መሆኑን ገልጸዋል።

በተቀረጸው የንግድ ሪፎርም መሠረትም በርካታ የገበያ መሠረተ ልማቶች እየተገነቡ ይገኛሉ ብለዋል።
በዚህም በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ቁጥር 1ሺህ 950 በላይ መድረሱን ተናግረው፤ እነዚህን ገበያዎች ደረጃቸውን የጠበቁ የማድረግ ሥራ በትኩረት እየተከናወነ ነው ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት በተለያዩ አካባቢዎች ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ ወጪ 10 የሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከላት እየተገነቡ መሆኑንም ገልጸዋል።

ዛሬ የተመረቀው የሰመራ ማዕከልም ከ70 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት መሆኑን በመጠቆም።
ኢትዮጵያ ከሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ወዲህ ከቁም እንስሳት ዘርፍ የምታገኘው ገቢ እያደገ መምጣቱንም ጠቁመዋል።
በ2017 በጀት ዓመት ከዘርፉ 60 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን አስታውሰው፤ በያዝነው በጀት ዓመት ባለፉት ስምንት ወራት ብቻ 39 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን አስታውቀዋል።

የአፋር ክልል የእንስሳት ሀብት ለሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ግኝት ትልቅ አቅም ያለው መሆኑን ገልጸው፤ የማዕከሉ መገንባት የለውጡ መንግሥት ለአርብቶ አደሩ ያለውን ውግንና በተግባር ያረጋገጠበት ነው ብለዋል።
ማዕከሉ ወደ ሥራ መግባቱ የአርብቶ አደሩንና የነጋዴውን ተጠቃሚነት በማሳደግ በኩል ትልቅ ሚና ያለው መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል።
የአፋር ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አወል አርባ በበኩላቸው፤ የማዕከሉ ወደ ስራ መግባት በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀብት ወደ ላቀ የኢኮኖሚ ጥቅም መለወጥ ያስችላል ብለዋል።
ማዕከሉ በተያዘለት ጊዜ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት መብቃቱን ጠቁመው፤ ይህም መንግሥት ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረትና የኢኮኖሚ አካታችነት ማሳያ መሆኑን አብራርተዋል።
ማዕከሉ ለሚሌ (Quarantine) የእንስሳት ማቆያ ቅርበት ያለው በመሆኑ፣ የእንስሳት ወጪ ንግድን ለማሳለጥና የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግ ትልቅ አበርክቶ አለው ብለዋል።
አርብቶ አደሩ የእንስሳት ሃብቱን በቀጥታ ለገበያ እንዲያቀርብ ምቹ ሁኔታ ከመፍጠሩ በላይ፣ በዘርፉ ለተሰማሩ ነጋዴዎች ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ነው ያሉት።
ማዕከሉ ለእንስሳት ግብይት የሚያስፈልጉ ሁሉንም ዓይነት መሠረተ ልማቶች አሟልቶ የተገነባ በመሆኑ ግብይቱ ቀልጣፋና ሥርዓት ያለው እንዲሆን ያስችላል ሲሉ አረጋግጠዋል።
የዚህ ማዕከል መከፈት የቁም እንስሳት ንግድ ዳግም እንዲያንሰራራ እንደሚያደርግ ጠቁመው የእንስሳት ግብይት እንዲሳለጥና ውጤታማ እንዲሆን ከክልሉ መንግሥት የሚጠበቅብንን ሁሉ እናደርጋለን ብለዋል።
አምቦ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን የፍራፍሬ ልማትን የማስፋፋት ስራ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር ገለጸ።...
Mar 27, 2026
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ ያቀረበችው እ.አ.አ 2003 ነበር። ኢትዮጵያ በወቅቱ ጥያቄውን ካቀረበች በ...
Mar 27, 2026
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025