🔇Unmute
አዲስ አበባ፤መጋቢት 23/2018 (ኢዜአ)፦የቻይና ባንክ (Bank of China) በቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ፕሮጀክት ላይ ለመሳተፍ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ።
ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ እና ከገንዘብ ሚኒስቴር የተወጣጣ የኢትዮጵያ ልዑክ፣ ስለ አዲሱ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ግንባታ የገንዘብ ድጋፍ ዙሪያ ከቻይና ባንክ ጋር ውይይት አድርጓል።
በውይይቱ ወቅት የኢትዮጵያ ልዑክ ስለ ፕሮጀክቱ ቴክኒካዊ ንድፍ (design)፣ስለ ግንባታው የጊዜ ሰሌዳ እና ስለ አጠቃላይ የፋይናንስ መዋቅሩ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥቷል።
በተጨማሪም ፕሮጀክቱን ይበልጥ ውጤታማ፣በባንኮች ዘንድ ተቀባይነት ያለው (bankable) እና በረጅም ጊዜ የሀገሪቱን የፋይናንስ አቅም የማይጎዳ ለማድረግ የተከናወኑ የማሻሻያ ስራዎችን በተመለከተ ገለጻ ተደርጓል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በበኩሉ ፕሮጀክቱ በቀጣናው ያለውን ከፍተኛ ፋይዳ በአጽንኦት ያነሳው ጉዳይ ነው።
አዲሱ አየር ማረፊያ ኢትዮጵያ በአቪዬሽን ዘርፍ ያላትን መሪነት የሚያጠናክር ከመሆኑም በላይ ለንግድ፣ ለቱሪዝም እና ለአጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገት ያለውን ሚና ልዑኩ አስረድቷል።
የቻይና ባንክ በፕሮጀክቱ ላይ ለመሳተፍ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው ገልጿል።
ባንኩ በአየር ማረፊያ ኢንቨስትመንቶች ላይ ልምድ እንዳለው ገልጾ፥ በአፍሪካ ከፍተኛ ተጽዕኖ ፈጣሪ በሆኑ መሰረተ ልማቶች ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ አመልክቷል።
የአየር ማረፊያ ፕሮጀክት ከባንኩ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች እና በትላልቅ የትራንስፖርት መሰረተ ልማት ፋይናንስ ካለው ልምድ ጋር በሚገባ እንደሚጣጣምም ነው ባንኩ ያስታወቀው።
በተጨማሪም ባንኩ የፕሮጀክቱ ዋና አስተባባሪ (Mandated Lead Arranger) ከሆነው ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር የፋይናንስ ማዕቀፉን ለመረዳት እና በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ዙሪያ እየተነጋገረ መሆኑን ጠቁሟል።
ውይይቱ በዋናነት የገንዘብ ድጋፍ በሚደረግበት ሁኔታ፣ ከሌሎች አበዳሪዎች ጋር በሚኖር ቅንጅት እና አስፈላጊ በሆኑና ጥንቃቄ በሚሹ መስፈርቶች ላይ በማተኮር ተካሄዷል።
ሁለቱም ወገኖች የቴክኒክ እና የፋይናንስ ውይይቶችን በተጠናከረ ሁኔታ ለማስቀጠል እና የቅርብ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማምተዋል።
የቻይና ባንክ በገንዘብ ድጋፍ ጥቅሉ ውስጥ ለመሳተፍ ዝግጁ እንዲሆን ቀጣይነት ያለው የመረጃ ልውውጥ እና የጋራ ጥረት አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
በውይይቱ የቻይና ባንክ ለፕሮጀክቱ የፋይናንስ አቅርቦት ድጋፍ በማድረግ የበኩሉን እንደሚወጣ መግለጹን የገንዘብ ሚኒስቴር ለኢዜአ በላከው መረጃ አመልክቷል።
ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...
Sep 11, 2026
ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...
Sep 10, 2026
ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...
Sep 7, 2026
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...
Aug 31, 2026