🔇Unmute
ሰመራ፣መጋቢት 26/2018 (ኢዜአ) ፡-በምርምር ስራዎች የአደጋ ተጋላጭነትን ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት ማጠናከር እንደሚገባ የሠመራ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ዓሊ ተናገሩ።
በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለዘጠነኛ ጊዜ የተዘጋጀ የአደጋ ተጋላጭ ማህበረሰብ ዝግጁነትና መቋቋም ላይ ያተኮረ ሲምፖዚየም በሰመራ ከተማ ተካሄዷል።

በመድረኩ ላይ ምክትል ፕሬዚዳንቱ እንደተናገሩት፤ የምርምር ስራዎችን በማጠናከርና ተግባራዊ በማድረግ የአደጋ ተጋላጭነትን ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት መደገፍ ይገባል።
የምርምር ውጤቶቹ ማህበረሰቡን ከማንቃትና ተጋላጭ እንዳይሆኑ ከማድረግ አኳያ ሚናው ከፍተኛ መሆኑን አስረድተዋል።
በተለይም ተመራማሪዎች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት የአካባቢውን ችግር ተረድተው እገዛ ሊያደርጉ እንደሚገባ አመልክተው በአካባቢው የሚገነቡ ህንፃዎች ጭምር ግምት ውስጥ ሊገቡ እንደሚገባም አመልክተዋል።
በሲምፖዚየሙ ላይ የተገኙት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመሬት መንቀጥቀጥ ተመራማሪና መምህር ፕሮፌሰር አታላይ አየለ በበኩላቸው፤ የተፈጥሮ አደጋዎች ከመከሰታቸው በፊት ዝግጅት ማድረጉ የጉዳት መጠኑን ለመቀነስ እገዛ ያደርጋል ብለዋል።

የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት ውሳኔ ሰጪ አካላት ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡ ማድረግ፣ ፖሊሲዎችን ማጤንና የህንፃ ግንባታ ደረጃ ግልፅ መሆን እንዳለበት ተናግረዋል።
መገናኛ ብዙሃን ጉዳዩን አስመልክተው እያከናወኑ ያለው የግንዛቤ ማስጨበጥ ተግባር ሊጠናከር እንደሚገባ ጠቁመው የምርምር ግኝቶችን በየጊዜው በማውጣት ለሚመለከታቸው አካላት ማጋራት ይገባል ብለዋል።
በመድረኩም ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የመጡ ተመራማሪዎች፣ የትምህርት ሚኒስቴርና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...
Sep 11, 2026
ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...
Sep 10, 2026
ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...
Sep 7, 2026
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...
Aug 31, 2026