🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦የከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት መርሃ ግብር የዜጎችን የሥራ ባህል ቀይሯል፣ ገቢ ጨምሯል፣ ከተረጅነት አውጥቷል፡፡
በኢትዮጵያ ልማታዊ ሴፍትኔት በ1997 ዓ.ም፤ የከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት ደግሞ በ2009 ዓ.ም በይፋ ሥራ ከተጀመረ ወዲህ በሚሊዬን የሚቆጠሩ ዜጎችን በቀጥታና በተዘዋዋሪ ተጠቃሚ አድርጓል፡፡
መርሃ ግብሩ ዜጎችን በከተማ ውበትና ጽዳት፡ በደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ በከተማ ግብርናና አረንጓዴ ልማት በማሰማራት ገቢያቸውን ለማሻሻልና የምግብ ዋስትናቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል ስትራቴጂ ነው፡፡

በዚህም በርካታ ዜጎችን በየሶስት ዓመቱ የምርቃት ሂደትን በማሳለፍ ሀብት እንዲፈጥሩና ከተረጅነት እንዲላቀቁ አስችሏል፡፡
በአዲስ አበባ ኢዜአ ያነጋገራቸው የከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት ተጠቃሚዎች እንዳሉት፤ መርሃ ግብሩ በአካባቢያቸው በልማት ስራዎች የሚሳተፉበትን ዕድል ፈጥሯል፡፡
መርሃ ግብሩ ተጠቃሚዎችን ከጊዜያዊ ድጋፍና ተረጅነት በማላቀቅ የራሳቸው ቋሚ የገቢ ምንጭ እንዲኖራቸው ማስቻሉን ገልጸዋል፡፡
ወይዘሮ ጸሀይ ገላው በመዲናዋ መንገድ ላይ እጣን በመሸጥ ይተዳደሩ እንደነበር በማንሳት፤ የከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት የህይወታቸው መድህን እንደሆነ ያስታውሳሉ፡፡

ዛሬ ታሪክ ተቀይሮ በአዋቂዎችና ሕፃናት አልባሳት ሽያጭ የንግድ ዘርፍ ተሰማርተው ራሳቸውን ከተረጅነት በማላቀቅ ቤተሰቦቻቸውን ማስተዳደር መቻላቸውን ይገልፃሉ፡፡
በቀጣይ ንግዳቸውን በማስፋት ገቢያቸውን የማሳደግ እንዲሁም ለሌሎች የሥራ ዕድል የመፍጠር እቅድ እንዳላቸው ገልጸው፤ ለተደረገላችው ድጋፍ አመስግነዋል።
መንገድ ላይ እንቁላል በመሸጥ ራሷንና ቤተሰቧን ታስተዳድር የነበረችው ወጣት ሰኢዳ ሀሰን፤ መንግሥት በመርሃ ግብሩ በማሳተፍ ተጠቃሚ እንዳደረጋት ገልፃለች፡፡

በከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት መርሃ ግብር በተሰጣት ገንዘብ በዶሮ እርባታና በምግብ ቤት ንግድ ዘርፍ በመሰማራት ህይወቷን መቀየሯን አስረድታለች፡፡
በሥራዬ ከቤተሰቤ አልፎ ለአካባቢ ማህበረሰብ ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረብኩ ነው የምትለው ወጣት ሰኢዳ፤ ተግቶ መሥራትን የሚያበረታታ መርሃ ግብሩ መሆኑን ገልጻለች፡፡
በአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ የከተማ ልማታዊ ሴፍትኔትና ሥራ ፕሮጀክት አስተባባሪ ተመስገን ሙሉዓለም (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ዜጎች በፈለጉት የሥራ መስክ ሰልጥነው እንዲሰማሩ የሚያስችል መርሃ ግብር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ዜጎች በአምስት የሥራ ዘርፎች ተሰማርተው ራሳቸውን በመቻል ከተረጅነት እንዲውጡ እንደሚያስችል ገልጸው፤ መርሃ ግብሩ ተጠቃሚዎች ወደ ዘላቂ የኑሮ ማሻሻያ እንዲሸጋገሩ ያግዛል ብለዋል፡፡
ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...
Sep 11, 2026
ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...
Sep 10, 2026
ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...
Sep 7, 2026
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...
Aug 31, 2026