🔇Unmute
ጂንካ፤ መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦የለውጡ መንግስት ለከተሞች እኩል የመልማት ዕድልን ማስገኘቱን የጂንካ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ።
የለውጡ መንግስት አሰባሳቢ ትርክትን የመገንባት ተግባር በትኩረት አከናውኗል
የለውጡን 8ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በጂንካ ከተማ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው፡፡

የድጋፍ ሰልፉ በለውጡ ዓመታት ለተገኙ ትሩፋቶች፣ አንፀባራቂ ድሎች እና ሀገራዊ ስኬቶች ዕውቅና በመስጠትና ለማስቀጠል ያለመ ነው።
በድጋፍ ሰልፉ የተሳተፉ የጂንካ ከተማ ነዋሪዎች ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት በሀገራዊ ለውጡ ከሌሎች ከተሞች እኩል የመልማት ዕድል ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

ከድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች መካከል አቶ አበራ ገብረስላሴ የለውጡ ዓመታት እንደ ሀገር አስደማሚ ስኬቶች የተመዘገቡበት ስለመሆኑ አንስተዋል።
ከተመዘገቡ ስኬቶች አንዱ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መሆኑን አንስተው፥ በተለይ በከተሞችና በገጠር አካባቢ የተጀመሩ የኮሪደር ልማቶችና ሜጋ ፕሮጀክቶች የለውጡ ትሩፋት ማሳያዎች ናቸው ብለዋል።
ቀደም ሲል እንደ ጂንካ ያሉ የጠረፍ ከተሞች የተዘነጉ በመሆናቸው ዕድገታቸው አዝጋሚ እንደነበር ያስታወሱት ደግሞ አቶ ታዲዮስ ቡቼ ናቸው።

ከለውጡ ዓመታት ወዲህ እንደ ጂንካ ከተማ ያሉ የተረሱ ከተሞች ሁሉ የመልማት እድል አግኝተዋል ብለዋል።
የለውጡ መንግስት ሀገር ከገባችበት ውስብስብ ችግር በማውጣት አስደማሚ ስኬት ማስመዝገቡ የሚደነቅ ነው ያሉት ደግሞ ወይዘሮ አማረች አምባው ናቸው።

ሀገራዊ ለውጡ ሁለንተናዊ ለውጥ ማምጣት የሚያስችል አቋም እንዲኖረን አድርጓል ያሉት ወይዘሮ አማረች፥ በለውጡ ዓመታት ትልቅ ኢኮኖሚ አቅም የተገነባበት ነው ብለዋል።
በተለይ ወጣቱ በሀገሩ ሰርቶ የሚለወጥበትና ሀብት የሚያፈራበት ዕድል መፈጠሩንም ገልጸዋል።
በለውጡ ዓመታት በተለይ የሴቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ተረጋግጧል ያሉት ደግሞ ወይዘሮ የምስራች ታደለ ናቸው።

ሴቶች ከጥገኝነት ተላቀው በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካው እና በማህበራዊ ኑሮ መሪ ተዋናይ የሚሆኑበት አውድ ተፈጥሯልም ብለዋል።
ሀገራዊ ለውጡ የአሁኑን ትውልድ ብቻ ሳይሆን የመጪውንም ትውልድ ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ጠቁመው፥ ይህም ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ነው ብለዋል።
በድጋፍ ሰልፉ ላይ የጂንካ ከተማ ነዋሪዎችን ጨምሮ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ የአሪ ዞን እና የጂንካ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ታድመዋል።
ባህር ዳር፤ ሰኔ 2/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል የማዕድን ሀብት ልማት ዘርፉ በጥናትና ምርምር በመታገዙ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል እየፈጠረና ከፍተኛ የገቢ...
Jun 10, 2026
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 1/2018 (ኢዜአ)፦ ህዝባችን ለአገልግሎት ፍለጋ ጊዜና ገንዘቡን ሳያባክን ሃብቱን ለልማት እንዲያውል የምናደርገውን ጥረት አጠናክረን እንቀጥ...
Jun 9, 2026
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 19/2018 (ኢዜአ)፦ የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ መመረቅ ፍትሐዊና ሚዛናዊ የመሠረተ ልማት ዝርጋታን የሚያረጋግጥ መሆኑን ጠቅላ...
May 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/2018 (ኢዜአ)፡- ቱሪዝም የኢኮኖሚያችን አንዱ ምሰሶ እንደመሆኑ የሀገራዊ ዕድገታችንን የወደፊት አቅጣጫ እየቀረጸ ያለ ዘርፍ መሆኑ...
Apr 20, 2026