🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦ ለትንሳኤ በዓል በቂ የእንስሳትና የእንስሳት ተዋጽኦ ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ ለማህበረሰቡ እያቀረበ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ገለጸ።
በመዲናዋ ለመጪው የትንሳኤ በዓል ፍጆታ የሚውሉ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች በስፋት ወደ ገበያ እየቀረቡ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽነር ባዩ ሽጉጤ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ለበዓል ፍጆታ በቂ የእንስሳትና የእንስሳት ተዋፅኦ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እያቀረብን ነው ብለዋል።
የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ የገበያ መረጋጋት ለመፍጠርና በኅብረተሰቡ ፍላጎት ልክ በቂ ምርት ለመቅራብ ሰፊ ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀዋል።
በተለይ በበዓሉ የተለያዩ የእንስሳት ተዋፅኦ ምርቶችን ህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲሸምት ዝግጅት በማድረግ ወደ ሥራ መግባቱን አንስተዋል፡፡
በዚህም ለበዓሉ ፍጆታ የሚውሉ እንደ እንቁላል፣ ቅቤ፣ አይብ፣ ዶሮና የደለቡ በሬዎች በበቂ ሁኔታ እና በተመጣጣኝ ዋጋ መቅረብ መጀመራቸውን አስታውቀዋል።

እነዚህ ምርቶች በከተማዋ በተዘጋጁ ባዛሮችና ኤግዚቢሽኖች እንዲሁም በእንስሳት ልማትና ልህቀት ማዕከል ስር በሚገኙ ሱቆች ለተጠቃሚው እየቀረቡ መሆኑን ተናግረዋል።
የእንስሳት ልማትና ልህቀት ማዕከል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አሌክስ ደመቀ በበኩላቸው፤ ማዕከሉ ጥራት ያላቸው ምርቶችን ለኅብረተሰቡ ተደራሽ እያደረገ ነው ብለዋል።

በኤልያስ፣ ይሳቅና ጓደኞቻቸው የወተት ተዋፅኦ ህብረት ስራ ማህበር የሽያጭ ባለሙያ የሆኑት የሺወርቅ ዳኛቸው ለበዓሉ የሚፈለጉ የቅቤና አይብ ምርቶች በስፋት ማቅረባቸውን ተናግረዋል።
ሰላም የዶሮ እርባታ እና የእንቁላል ሽያጭ ሽርክና ማህበር ተወካይ ብርቅነሽ ዳባ እንቁላልን ጨምሮ የበዓል ፍጆታ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እየሸጡ መሆኑን ገልጸዋል።
ባህር ዳር፤ ሰኔ 2/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል የማዕድን ሀብት ልማት ዘርፉ በጥናትና ምርምር በመታገዙ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል እየፈጠረና ከፍተኛ የገቢ...
Jun 10, 2026
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 1/2018 (ኢዜአ)፦ ህዝባችን ለአገልግሎት ፍለጋ ጊዜና ገንዘቡን ሳያባክን ሃብቱን ለልማት እንዲያውል የምናደርገውን ጥረት አጠናክረን እንቀጥ...
Jun 9, 2026
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 19/2018 (ኢዜአ)፦ የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ መመረቅ ፍትሐዊና ሚዛናዊ የመሠረተ ልማት ዝርጋታን የሚያረጋግጥ መሆኑን ጠቅላ...
May 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/2018 (ኢዜአ)፡- ቱሪዝም የኢኮኖሚያችን አንዱ ምሰሶ እንደመሆኑ የሀገራዊ ዕድገታችንን የወደፊት አቅጣጫ እየቀረጸ ያለ ዘርፍ መሆኑ...
Apr 20, 2026