🔇Unmute
አዳማ ፤ ሚያዚያ 5/2018 (ኢዜአ)፦ በአርሲ ዞን የዴራ ከተማ ወጣቶች ከስደት ተመልሰው በተሰማሩበት የእንስሳት እርባታ ውጤታማ መሆናቸውን ገለጹ።
ከስደት ተመላሾቹ መካከል ወጣት ሳዲቅ ሲራጅ እንደገለጸው በሕገወጥ መንገድ ባሕር አቋርጦ ዓረብ አገር ለረጅም ጊዜ ቢሠራም ውጤት አላገኘም።

ከስደት ሕይወቱ ትምህርት በመውሰድ በሀገሩ ሠርቶ የመለወጥ ዓላማን በመያዝ፣ መንግሥት ባመቻቸለት የሥራ ዕድል በመጠቀም በወተት ላሞች እርባታ መሰማራቱን ገልጿል።
በዚህም የተሻሻሉ ዝርያ ያላቸውን ላሞችን በግል መኖሪያ ቤቱ በማርባት የጀመረውን ሥራ በማሳደግ፣ ከዴራ ከተማ አስተዳደር በተረከበው በ350 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የወተት ላሞች እርባታ ማዕከል መገንባቱን አስረድቷል።

ይህም የወተት ምርቱን ለከተማዋ ነዋሪዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ እንዳስቻለው ጠቅሷል።
ሌላኛው ከስደት ተመላሽ ወጣት ነቢዩ አብዱላሂ በበኩሉ፣ ከባለቤቱ ጋር ሠርተው መለወጥን በማሰብ በሕገወጥ መንገድ ዓረብ አገር በመሄድ ለዓመታት ያለ ውጤት ማሳለፋቸውን ያስታውሳል።

በስደት በቆዩበት ዓመታት ያጡትን ውጤት ሀገራቸው ሠርተው ለመለወጥ የመንግሥትን የሥራ ፈጠራ ዕድል መጠቀማቸውን ጠቁመዋል።
በአሁኑ ወቅትም በማኅበር ተደራጅተው በዶሮ እርባታ ሥራ ላይ በመሰማራት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ማሳደጋቸውን ገልጸዋል።
በዚህም 3 ሺህ የአንድ ቀን ጫጩቶችን በማስፈልፈል ለሌሎች ማኅበራት ማቅረባቸውን ተናግረዋል።

ሥራቸውን ለማሳደግም መንግሥት የዶሮ እርባታ ማዕከላትን ገንብቶ ከመስጠቱም ባለፈ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ብድር ማግኘታቸውንም ገልጸዋል።
በሕገወጥ መንገድ ወደ ውጭ የሚጓዙ ወጣቶች ለአካል ጉዳትና ለሞት አደጋ ጭምር የሚጋለጡ በመሆኑ በሀገራቸው ሠርተው መለወጥ እንደሚቻል አስረድተዋል።
የዴራ ከተማ ከንቲባ አቶ ኑራ ሁሴን በበኩላቸው አስተዳደሩ ከ300 በላይ የወተት ላሞችና የዶሮ እርባታ እንዲሁም የማድለቢያ ማዕከላት በመገንባት በማኅበር ለተደራጁ ወጣቶች በማስተላለፍ ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

በተለይ የከተማ ግብርናን ለማስፋፋትና ውጤታማ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ጠቅሰው፤ በወተት ልማትና በዶሮ እርባታ እንዲሁም በማድለቢያ ሥራ የተሰማሩ ወጣቶች ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገቡ ይገኛሉ ብለዋል።
በከተማ ግብርና የተሰማሩ አንቀሳቃሾች ኢኮኖሚያዊ አቅማቸውን ከማሳደግ ባለፈ ለከተማዋ የገበያ መረጋጋት ማገዛቸውን ገልጸዋል።
ጅማ፤ ሚያዝያ 6/2018(ኢዜአ)፡- በጅማ የኮደርስ ስልጠና የወሰዱ የመንግሥት ሠራተኞች ቀልጣፋና ዘመናዊ የሕዝብ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ እያገዛቸው መሆኑን...
Apr 14, 2026
አምቦ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን የፍራፍሬ ልማትን የማስፋፋት ስራ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር ገለጸ።...
Mar 27, 2026
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ ያቀረበችው እ.አ.አ 2003 ነበር። ኢትዮጵያ በወቅቱ ጥያቄውን ካቀረበች በ...
Mar 27, 2026
Jul 17, 2025