የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

መንግስት የግል ባለሃብቶች በኢንደስትሪ ፓርኮች ኢንቨስትመንት እንዲሰማሩ ያበረታታል

Apr 16, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2018 (ኢዜአ)፦ መንግስት የግል ባለሃብቶች በኢንደስትሪ ፓርኮች ኢንቨስትመንት እንዲሰማሩ እንደሚያበረታታ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

“የሉዓላዊነት ልብ” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ቆይታ አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከለውጡ ወዲህ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ብዛት እና ቁጥር ላይ ብቻ ሳይወሰኑ ጥራት ላይ እንዲያተኩሩ፣ በቅንጅት እንዲሰሩ መንግስት አመቻች ሆኖ እየሰራ መሆኑን ገልፀው፤ አሁን ካሉት 26 ኢንደስትሪ ፓርኮች ሰባቱ የግል መሆናቸውን ተናግረዋል።

የግል ኢንደስትሪ ፓርክ እየሰፋ መሄድ እንዳለበት አቋም መያዙን ተናግረው ኤ ኤም ጂ ን እና ኦዳን ለአብነት አንስተዋል፡፡

የግል ኢንደስትሪ ፓርኮች ብረትን በማቅለጥ፣ የመኪና መለዋወጫን በመስራትና ከባድ ኢንደስትሪ ላይ ማተኮራቸውን ተናግረው ኢንደስትሪዎቹ በስፋት፣ በቅንጅት፣ በሚያመርቱት ምርትና በውጤታቸውም የተሻሉ ናቸው ብለዋል፡፡

ኢንቨስትመንትን ለመሳብ፣ የመሰረተ ልማት ወጪን በመቀነስ፣ ቅንጅት በመፍጠር አንዱ ለአንዱ ግብአት በመሆንም ተመራጭ መሆናቸውን አብራርተዋል፣ የኢንደስትሪ ፓርክም ለኢምፖርት ኤክስፖርት አመቺነት ባለው ቦታም እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡

ከለውጡ በፊት የኢንደስትሪ ፓርኮች ህንፃ ግንባታ ላይ ብቻ ይተኮር እንደነበር ገልፀው፤ የውስጥ አቅም ያልገነባ፣ ወጪያቸው ከፍተኛ፣ የአዋጭነት ሁኔታቸው ያልተጠና እና ለብክነት ተጋላጭ ነበሩ ብለዋል፡፡

ከለውጡ ወዲህ የውስጥ አቅምን በመጠቀም የግንባታ ወጪን መቀነስ መቻሉን ስራ ማስጀመር እና ምርታማነት ላይ መተኮሩንም ተናግረዋል ፡፡

በዚህም ምርታማነት ማደጉንና አሁንም መሻሻል እንደሚገባው ተናግረዋል፡፡

ኤክስፖርት ከለውጡ በፊት ከነበረበት 51 ሚሊየን ዶላር በቀጣይ አመት ወደ 1 ቢሊየን ዶላር ያድጋል ተብሎ እንደሚጠበቅም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026

በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል

ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...

Sep 7, 2026

በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...

Aug 31, 2026