የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

በክልሉ ከ919 ሺህ የሚበልጡ ዜጎች በተለያዩ መስኮች የስራ እድል አገኝተዋል

Apr 20, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ባህር ዳር፤ ሚያዚያ 10/2018 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ከ919 ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች በተለያዩ መስኮች የስራ እድል መፈጠሩን የክልሉ ስራና ስልጠና ቢሮ ገለጸ።

‎የቢሮው የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተር ፕራይዞች ልማት ዳይሬክተር አቶ ስላባት ሰውአገኝ ለኢዜአ እንደገለፁት ዜጎችን የስራ እድል ተጠቃሚ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው።

በዚህም በበጀት ዓመቱ አንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን ለሚጠጉ ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር ግብ ተይዞ በተደረገ ሁሉን አቀፍ ጥረት በዘጠኝ ወሩ ለ919 ሺህ 475 ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉን ገልፀዋል።

የስራ ዕድሉ ከተፈጠረባቸው መስኮች መካከልም ከ125 ሺህ 300 በላይ የሚሆኑት በውጭ ሀገር የስራ ስምሪት መሆኑን ገልጸዋል።

የስራ ዕድሉ በግብርና፣ በኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፎች መሆኑን ገልጸው፤ በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት በድምሩ ለ919 ሺህ 475 ዜጎች የስራ ዕድል ተፈጥሯል ብለዋል።

ዳይሬክተሩ እንዳሉት 1 ሺህ 347 የመስሪያ ሼዶች እንዲሁም ለከተማ ግብርና፣ ለማዕድን ማውጫና ለሌሎች የግብርና ልማት ተግባራት 11 ሺህ 444 ሄክታር መሬት ለኢንተርፕራይዞች መተላለፉንም ተናግረዋል።

‎የመስሪያ ገንዘብ ለሚያስፈልጋቸው ኢንተርፕራይዞች ከ5 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ የብድር አቅርቦት የተመቻቸ ስለመሆኑም አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026

በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል

ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...

Sep 7, 2026

በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...

Aug 31, 2026