🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 12/2018 (ኢዜአ) ፦ ኢትዮጵያ እና እንግሊዝ በልማት እና በኢንቨስትመንት ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር ተስማምተዋል።
በዋሺንግተን ዲሲ ሲካሔድ ከቆየው የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) እና የዓለም ባንክ ዓመታዊ የፀደይ ወቅት ስብሰባ ጎን ለጎን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ ከእንግሊዙ ዓለም አቀፍ ልማት ሚኒስትር ባሮኒስ ቻፕማን ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለውን የልማት የንግድ እና የኢንቨስትመንት ትብብርና አጋርነት ለማጠናከር ተስማምተዋል።

አቶ አህመድ ሽዴ በኢትዮጵያ ያለውን ጠንካራ የኢኮኖሚ ሪፎርም ሂደትና የተገኙ ስኬቶችን በተመለከተ ገለጻ አደርገዋል።
ኢትዮጵያ ከእንግሊዝ ጋር ያላትን ጠንካራ አጋርነት ያነሱት ሚኒስትሩ የእንግሊዝ መንግስት የሚያደርገውን ድጋፍ አንዲያጠናክርም ጠይቀዋል።
ባሮኒስ ቻፕማን በበኩላቸው ኢትዮጵያ እያካሔደች ያለውን የለውጥ ስራ በማድነቅ የእንግሊዝ መንግስት የልማት አጋርነቱን ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል።
ሚኒስትሯ አያይዘውም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት ዙሪያ ያላትን ቁልፍ ሚና አንስተዋል።
ሁለቱ ወገኖች በውይይታቸው የሃገራቱን አጋርነት ከማስፋት ባለፈ በንግድ ፣ በልማትና በኢንቨስትመንት እንዲሁም በኢኮኖሚ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማምተዋል።
ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...
Sep 11, 2026
ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...
Sep 10, 2026
ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...
Sep 7, 2026
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...
Aug 31, 2026