🔇Unmute
ነጌሌ ቦረና፤ ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡- በምሥራቅ ቦረና ዞን ለ450 ሺህ የቤት እንስሳት የክትባት አገልግሎት በዘመቻ መልክ እየተሰጠ መሆኑን የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ገለጸ፡፡
በጽሕፈት ቤቱ የእንስሳት ጤና ባለሙያ በነያ አሬሮ ለኢዜአ እንዳሉት፤ እየጣለ ያለውን የበልግ ዝናብ ተከትሎ ሊቀሰቀስ የሚችለውን የእንስሳት በሽታ አስቀድሞ ለመከላከል የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው።

440 የእንስሳት ሐኪሞችና በርካታ ድጋፍ ሰጭ ሠራተኞች ለእንስሳቱ ክትባት እየሰጡ መሆኑንም ገልጸዋል።
በዞኑ ስምንት ቆላማ ወረዳዎች በሚካሄው የእንስሳት ክትባት ዘመቻ፤ 450 ሺህ የቤት እንስሳትን ተደራሽ ለማድረግ ታቅዷል ብለዋል።
እስካሁንም ለ60 ሺህ 849 የቤት እንስሳት የክትባት አገልግሎት መሰጠቱን ጠቅሰው፤ የክትባት አገልግሎቱ በዋናነት እየተሰጠ ያለው ለግመሎች፣ ለዳልጋና ለጋማ ከብቶች እንዲሁም ለበግና ፍየሎች መሆኑን አብራርተዋል።

ክትባቱን ሙሉ በሙሉ ተደራሽ ለማድረግ 450 ሺህ ዶዝ የክትባት መድኃኒት መቅረቡን ተናግረዋል።
በተለይም ክትባቱ የሳንባ ምች፣ አባ ሰንጋ፣ አባ ጎርባና ሌሎችንም የእንስስት በሽታዎች አስቀድሞ ለመከላከል እንደሚያስችልም አስገንዝበዋል።
የክትባት አገልግሎቱ ተደራሽ መሆን፤ አርብቶ አደሩ እና ከፊል አርብቶ አደሩ ከእንስሳት ተዋፅዖ የሚያገኘውን ጥቅም ለማሳደግና የምግብ ዋስትናቸውን በዘላቂነት ለማረጋገጥ የጎላ ፋይዳ አለው ብለዋል።
ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...
Sep 11, 2026
ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...
Sep 10, 2026
ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...
Sep 7, 2026
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...
Aug 31, 2026