የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

የዩኒቨርሲቲው የጥናትና ምርምር ሥራዎች የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት እያሳደጉ ነው

Apr 29, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ወልቂጤ፤ ሚያዝያ 16/2018 (ኢዜአ)፦ከመማር ማስተማር ሥራው ጎን ለጎን እያካሄደ የሚገኘው የጥናትና ምርምር ስራዎች የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት እያሳደጉ መሆኑንየወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ።

የዩኒቨርሲቲው 7ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ ''በቴክኖሎጂ የታገዘ ምርምር ለዘላቂ ልማት፣ ጤና እና ሁሉን አቀፍ ደህንነት'' በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ነው።


በዚህ ወቅት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፋሪስ ደሊል (ዶ/ር) እንዳሉት ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ሥራው ጎን ለጎን ማህበረሰብ ተኮር የሆኑ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን በማከናወን ለውጤት እያበቃ ይገኛል።

በጤና አጠባበቅ፣ በግብርና፣ በታዳሽ የኃይል ሥርአት፣ በአስተዳደር፣ በትምህርት እና በሌሎች መስኮች ላይ የተለያዩ የጥናትና ምርምር ሥራዎች ማከናወኑንም ገልጸዋል።

የግብርና ምርታማነትን ለማሻሻል፣ የጤና አጠባበቅ ስርዓትን ለማጠናከር፣ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል እና የአካባቢ ጥበቃ ልማትን በዘላቂነት ለማስቀጠል የተከናወኑ እነዚህ የጥናት ውጤቶች የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት እያሳደጉ መምጣታቸውንም ተናግረዋል።

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዮሐንስ ገብሩ (ዶ/ር) በበኩላቸው የምርምር ኮንፈረንሱ ለሁለት ቀናት እንደሚቆይ ገልጸዋል።


በመድረኩም በሀገር ውስጥ ካሉ 16 ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ተመራማሪዎች ያከናወኗቸው 31 የጥናትና ምርምር ሥራዎች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል ብለዋል።

የጥናትና ምርምር ሥራዎቹ በግብርና፣ በጤና፣ በምህንድስና፣ በስነ-ምህዳር፣ በአካባቢ ጥበቃና መሰል መስኮች ላይ ማተኮራቸውን ገልጸው፣ የምርምር ውጤቶቹ በመድረኩ ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል ብለዋል።

ከጅማ ዩኒቨርሲቲ የመጡት ፕሮፌሰር ሱልጣን ሱሌይማን፤ ሀገር በቀል እውቀትን በመጠቀም ለሕክምና ምርምር እና ጤናን ለማሻሻል እየተሰራ ያለው ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ዩኒቨርሲቲዎች ሚናቸውን ሊያጠናክሩ ይገባል ብለዋል።


የምርምር ውጤቶቹ ወደ ታች ወርደው ጥቅም ላይ እንዲውሉ በጋራ መስራት እንደሚገባም አመልክተዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የፖሊሲ ጥናት እና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አክመል መሃመድ (ዶ/ር) በበኩላቸው እንዳሉት፤ ክልሉ በግብርና፣ በኢንዱስትሪ እና በአገልግሎት ዘርፍ የመልማት አቅም አለው።


ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመሆን የሚካሄዱ የጥናትና ምርምር ሥራዎች የክልሉን እድገት ለማፋጠን እያገዙ መሆኑን አንስተዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች ባከናወኗቸው ዘርፈ ብዙ የልማት ሥራዎች የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

ለዚህም ምሁራንና ፖሊሲ አውጪዎች በየደረጃው ካሉ የመንግስት አመራር አካላት ጋር ተቀራርበው በመስራት የምርምር ወጤቶችን በጋራ ገምግመው ጥቅም ላይ እንዲያውሉ አቅጣጫ ተቀምጧል ብለዋል።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው ሀገር ዓቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ ላይ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተጋበዙ ምሁራንና አመራሮች በመሳተፍ ላይ ናቸው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026

በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል

ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...

Sep 7, 2026

በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...

Aug 31, 2026