የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

ግብርን በታማኝነትና በወቅቱ በመክፈል ልማትን ለማፋጠን የዜግነት ግዴታችንን እየተወጣን ነው- በድሬዳዋ ተሸላሚ ግብር ከፋዮች

Aug 28, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ድሬዳዋ፣ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ)፡-ግብርን በታማኝነትና በወቅቱ በመክፈል ልማትን ለማፋጠን የዜግነት ግዴታቸውን እየተወጡ መሆናቸውን በድሬዳዋ ዕውቅናና ሽልማት የተሰጣቸው ግብር ከፋዮች ገለጹ።

የድሬዳዋ አስተዳደር በ2016 እና በ2017 ዓ.ም ግብራቸውን በታማኝነት ለከፈሉ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ዕውቅናና ሽልማት ሰጥቷል።


ሽልማትና ዕውቅና የተሰጣቸው ግብር ከፋዮች ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ የመንግስት ግብርን በታማኝነትና በወቅቱ በመክፈል ለድሬዳዋ ሁለንተናዊ ዕድገት የድርሻቸውን እየተወጡ ናቸው፡፡

አስተዳደሩም ለታማኝ ግብር ከፋዮች በየዓመቱ ዕውቅናና ሽልማት መስጠቱ ግብር ከፋዩ የዜግነት ሀላፊነቱን በታማኝነትና በወቅቱ እንዲወጣ ተነሳሽነት እየፈጠረ መሆኑን ገልፀዋል።

ከተሸላማዊቹ መካከል በሆቴል ሥራ የተሰማሩት ኤፍራታ ሚካኤል ግብራቸውን በወቅቱና በታማኝነት በመክፈላቸው የተሰጣቸው ዕውቅና እና ሽልማት ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ነው።

የከፈሉት ግብር ለድሬዳዋም ሆነ ለሀገር እድገት ጠቀሜታ ስላለው የዜግነት ግዴታቸውን መወጣታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቁመዋል።

ግብርን በታማኝነት ከፍሎ የዜግነት ግዴታን መወጣት ለአዕምሮ ሰላም የሚሰጥና ስራን በራስ መተማመን ለመፈፀም ያስችላል ያሉት ደግሞ ሌላው ተሸላሚ አቶ አስቻለው ብሩ ናቸው።

የንግዱ ማህበረሰብ ግብሩን በወቅቱና በታማኝነት መክፈሉ የድሬዳዋን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልማቶች ለማፋጠን ስለሚያግዝ ተግባሩን ማጠናከር እንዳለበት አስረድተዋል።

ሌላው ተሸላሚ አቶ አሪፍ ጣሂር በበኩላቸው አስተዳደሩ የሰጣቸው የምስጉን ግብር ከፋይ ዕውቅናና ሽልማት የዜግነት ኃላፊነታቸውን ይበልጥ ለመወጣት እንዳነሳሳቸው አስታውቀዋል።

አስተዳደሩ ግብርን በቴክኖሎጂ መክፈል የሚያስችል አሰራር መዘርጋቱ የግብር ከፋዩን እንግልት ከማስቀረት ባለፈ ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኝ በማስቻሉ መቀጠል አለበት ብለዋል።

ባለፉት ዓመታት በድሬዳዋ ለተመዘገቡ አበረታች የልማት ውጤቶች የታማኝ ግብር ከፋዮች ድርሻ የጎላ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ናቸው።


በአስተዳደሩ የግብር አሰባሰቡን ለማዘመንና ለማቀላጠፍ ዲጂታል አሰራርን ተደራሽ የማድረግ ሥራ መከናወኑንም አስታውቀዋል።

አስተዳደሩ ታማኝ ግብር ከፋዮችን ከማበረታታት ባለፈ በህገ ወጦች ላይ ተገቢውን እርምጃ የመወሰዱ ሥራውን አጠናክሮ መቀጠሉንም አስታውቀዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ለታማኝ ግብር ከፋዮች የተዘጋጁ ሽልማቶችን አበርክተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሐረሪ ክልል በኢንቨስትመንት ዘርፍ የተፈጠረው ምቹ ሁኔታ ውጤታማ እያደረገን ነው -ባለሀብቶችና ወጣቶች

ሀረር፤ ነሐሴ 20/2018 (ኢዜአ)፡- በሐረሪ ክልል በኢንቨስትመንት ዘርፍ የተፈጠረው ምቹ ሁኔታ ውጤታማ እያደረጋቸው መሆኑን ባለሀብቶችና ወጣቶች ገለጹ። ...

Aug 27, 2026

የኢትዮጵያ የማዕድን ምርት እመርታ

በሙሴ መለሰ የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ በአገር በቀል የኢኮኖሚና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ታግዞ፣ ባለፉት ዓመታት የታዩበትን የአሰራርና መዋቅራዊ ችግሮች በመ...

Aug 22, 2026

የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር ዘላቂ ተጠቃሚነታችንን ለማረጋገጥ አስችሎናል-አርሶ አደሮች

ደብረብርሃን፤ ነሀሴ 14/2018 (ኢዜአ)፡-በሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር በመሳተፍ ዘላቂ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ መቻላቸውን አርሶ አደሮች ገለጹ። የሌማት ት...

Aug 21, 2026

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ከማዕድን ተገቢው ገቢ እንዲገኝ በትምህርት፣ በምርምር እና በአቅም ግንባታ ዘርፍ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ከማዕድን ተገቢውን ገቢ እንድታገኝ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት፣ በምርምር እና በአቅም ግንባታ ዘርፍ የ...

Aug 18, 2026