🔇Unmute
አዲስ አበባ፣መስከረም 15/2019 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ ሁለንተናዊ የገጠር ልማት እድገትን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እየሠራች መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ገለፁ።
ፕሬዝዳንት ታዬ ይህን ያሉት ከተመድ ጉባኤ ጎን ለጎን በተካሄደውና የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች፣የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሐመድ እና የዓለም አቀፉ የግብርና ልማት ፈንድ (IFAD) ፕሬዝዳንት አልቫሮ ላሪዮ በተገኙበት ከፍተኛ ደረጃ ስብሰባ ላይ ነው።
ፕሬዝዳንቱ በስብሰባው ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የግብርና ልማት ፈንድ (IFAD) ጋር ያላትን አጋርነት ለማጠናከር እየሠራች ነው።
ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የግብርና ልማት ፈንድ ጋር አምስት አስርተ ዓመታት የተሻገረ አጋርነት እንዳላትም ገልጸዋል።
ይህ አጋርነትም በገጠርና በከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የሚኖሩ ወደ 10 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎችን ህይወትና ኑሮ ማሻሻል ያስቻሉ ፕሮግራሞችን መተግበር ማስቻሉን አብራርተዋል።
እስካሁን በተከናወኑት የልማት ስራዎች የኢትዮጵያ መንግሥት የ227 ሚሊዮን ዶላር ቀጥታ አስተዋጽኦ ማድረጉንና በአጠቃላይ ወደ 1.2 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የጋራ ፈንድ (co-financing) ለልማት ስራዎች አውሏል ነው ያሉት።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም ኢትዮጵያ ለገጠር ልማት ሽግግርና ግብርና እድገት ያላትን ቁርጠኝነት ለማረጋገጥ ለፈንዱ ማደሻ ታቅዶ የነበረውን የ100 ሺህ ዶላር አስተዋጽኦ ወደ 1 ሚሊዮን ዶላር አሳድጋለች ብለዋል።
መቱ፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):- በኢሉባቦር ዞን ከቡና ምርት የሚገኘውን ገቢና የአካባቢውን አምራቾች ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ በቡና ጥራት አጠባበቅና...
Sep 23, 2026
አሶሳ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለውን የውሃ ሀብት ለመስኖ ልማት በማዋል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት ተጠና...
Sep 18, 2026
ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...
Sep 11, 2026
ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...
Sep 10, 2026