የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

ኢትዮጵያ እና ቡና

Oct 4, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ኢትዮጵያ- ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ ፤ታላቅ ርዕይ

በኢትዮጵያ የተገኘውና በዓለም ላይ የተስፋፋው ቡና ተቆልቶና ተፈጭቶ በብዛት የሚጠጣ ተፈለጊና ተወዳጅ ምርት በመሆን የዓለምን ገበያ ተቆጣጥሮት ይገኛል።

በተለይም በማደግ ላይ ባሉ አገሮችም እስከ 25 ሚሊዮን የሚደርሱ የአርሶ አደሮች የዓለምን 80 በመቶ ቡና እንደሚያመርቱ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያን ጨምሮ ብራዚል፣ ቪትናም እና ኮሎምቢያ ተጠቃሽ አገሮች ሲሆኑ ሌሎችም ይጠቀሳሉ።

በመሆኑም የቡናን ዓለም አቀፍ ግብይትና ተፈላጊነት እንዲሁም የተጠቃሚዎች ብዛት መሰረት በማድረግ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥቅምት 1 የዓለም የቡና ቀን አድርጎ ሰይሞታል። በዚሁ መሰረትም የመጀመሪያው የዓለም የቡና ቀን እ.ኤ.አ ከጥቅምት 1 ቀን 2015 ጀምሮ በመከበር ላይ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ቡና ለኢትዮጵያዊያን የገቢ ምንጭ ብሎም የባህል መገለጫ፣ የእንግዳ መቀበያ፣ የአብሮነት ማሳያ፣ የማኅበራዊ ትስስርና የውይይት መድረክም ነው።

የኢትዮጵያ ቡና በልዩ ልዩ የጣዕም የሚገለጽና በእጅጉም ተፈላጊ ምርት በመሆኑ በተለይም በአርሶ አደሮች ህይወትና አጠቃላይ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ ወሳኝ ድርሻ አለው።

በአንዳንድ አካባቢዎች ቡና ተፈልቶ ከአንድ እስከ ሶስተኛ ዙር የመጠጣት ልምድም አለ። ምንም እንኳን አጠራራቸውና ከእያንዳንዱ ዙር ጋር የሚያያዙ ትርጓሜዎች በአካባቢው ባህል መሠረት የሚለያይ ቢሆንም የመጀመሪያው “አቦል”፣ ሁለተኛው “ቶና” እንዲሁም ሶስተኛው “በረካ” እየተባለ ይጠራል።

የዚህ የቡና ስነ ስርአት ዋነኛ ዓላማ በተደጋጋሚ መጠጣት ሳይሆን በአንድነት መቆየትን፣ ለሌላው ጊዜ መስጠትንና የማኅበረሰብ ትስስርን የሚያጠናክሩ የባህል ምልክቶች ናቸው።

ከቡናው ጋር የሚቀርብ (የቡና ቁርስ) እንደየ ሁኔታው ፋንዲሻ፣ ቆሎ፣ ዳቦ ወይም ሌሎች ቀለል ያሉ ምግቦች የሚቀርቡ ሲሆን እጣን አጭሶ በመመራረቅ የሚጠጣም ይሆናል።

በዘመናዊው ዓለም ቡና የንግድ፣ የሥራና የመዝናኛ አካል ሆኗል። በቡና ቤቶች፣ በሥራ ቦታዎችና በዘመናዊ የቡና ማቅረቢያ ሥፍራዎች ሰዎች ይገናኛሉ። ሆኖም በኢትዮጵያ ባህላዊ የቡና ሥነ ሥርዓት ውስጥ ያለው ልዩ ትርጉም ከጣዕምና ከንግድ በላይ ይዘልቃል። ከቤት እስከ ጎረቤት ፤ ከታሪክ እስከ ትውልድ የቆየ ትስስር ያለው የኢትዮጵያን ልዩ መገለጫ ባህል ነው።

የቡና ባህላዊ ሥነ ሥርዓትን በማስተዋወቅ እንዲሁም የቡና ታሪክን ከተፈጥሮ ሃብት ጋር አጣምሮ በማሳየት የሀገሪቱን ባህላዊ ቅርስ ለዓለም ማስተዋወቅ ያስፈልጋል።

የኢትዮጵያ ቡና የባህል ይዘቱ እንዳለ ሆኖ ለሀገሪቷ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ በመሆን ለእድገትና ማንሰራራት ሁነኛ መሰረት እየሆነ ይገኛል።

የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የቡና ቀን የቡና ዘርፍ ለዘላቂ ልማት የሚኖረውን አስተዋጽኦ በማድረግ “ቡና የዘላቂ መፍትሄ አካል” በሚል መሪ ሃሳብ በዓለም አቀፍ ደረጃ በነገው እለት የሚከበር ይሆናል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በኢሉባቦር ዞን ከቡና ምርት የሚገኘውን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በቡና ጥራት አጠባበቅ ላይ ትኩረት ተሰጥቷል

መቱ፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):- በኢሉባቦር ዞን ከቡና ምርት የሚገኘውን ገቢና የአካባቢውን አምራቾች ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ በቡና ጥራት አጠባበቅና...

Sep 23, 2026

በክልሉ ያለውን የውሃ ሀብት ለመስኖ ልማት በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ይገባል - ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለውን የውሃ ሀብት ለመስኖ ልማት በማዋል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት ተጠና...

Sep 18, 2026

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026