የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

የህዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታት ለተጀመሩ ሥራዎች ስኬታማነት የድርሻችንን እንወጣለን -የድሬዳዋ ነዋሪዎች

Oct 8, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ድሬዳዋ፣ መስከረም 27/2019 (ኢዜአ)፡-በድሬዳዋ የህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመፍታት የተጀመሩ ተግባራት ስኬታማ እንዲሆኑ ከአስተዳደሩ ጎን ሆነው የድርሻቸውን እንደሚወጡ ነዋሪዎች ገለጹ።

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ በልማትና በመልካም አስተዳደር ተግባራት ላይ ዛሬ ከነዋሪዎች ጋር ተወያይተዋል።


በውይይቱ ላይ የተሳተፉ ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት ባለፉት አምስት ዓመታት በሁሉም ዘርፍ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች የነዋሪውን ጥያቄዎች እየፈቱ መምጣታቸውን ገልጸዋል።

በድሬዳዋ አስተዳደር የወረዳ 3 ነዋሪ አቶ ሊሞሬ ገንሳ እንዳሉት እስካሁን በተከናወኑ የልማት ሥራዎች የድሬዳዋን ጽዳትና ውበት ከማጉላት ባለፈ ለነዋሪዎቿ ምቹ የመኖሪያና የሥራ አካባቢ ለመፈጠር ተችሏል።

አዲሱ የድሬዳዋ አስተዳደርም እነዚህን ስኬቶች በላቀ ደረጃ ለማሳደግ የሚያከናውናቸውን ተግባራት በጉልበት፣ በዕውቀትና በገንዘብ በማገዝ የድርሻቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸው ተናግረዋል።

ሌላው ነዋሪ አቶ ሽመልስ እሼቱ በበኩላቸው አዲሱ አስተዳደር የህዝብን ፍላጎትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ያዘጋጀው ህዝባዊ መድረክ የሚበረታታና ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት መሆኑን ገልጸዋል።

እኛም ከአስተዳደሩ ግን በመሰለፍ በሰላም፣ በልማት እና በሁሉም መስኮች የድርሻችንን ለማበርከት ተዘጋጅተናል ብለዋል።

የወረዳ 3 ነዋሪዎች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ በአረንጓዴ አሻራ፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በልማት ፕሮጀክቶች ላይ ተቀናጅተው ኃላፊነታቸውን እየተወጡ መሆኑን የገለፁት ደግሞ ወይዘሮ መይሙና አህመድ እና ወይዘሮ አይናለም ማሞ የተባሉ ነዋሪዎች ናቸው።

አዲሱ አስተዳደር በተለያዩ አካባቢዎች የሚያከናውናቸው የልማት ፕሮጀክቶች ውጤታማ እንዲሆኑ ከአስተዳደሩ ጎን ሆነን በቁርጠኝነት እንሰራለን ብለዋል።

ወጣት በሐር አህመድ በበኩሉ ለድሬዳዋ የብልጽግና ጉዞ ወጣቱ በበጋ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት እና በዘላቂ ሰላም ላይ የድርሻውን እየተወጣ መሆኑን ገልጿል።


ውይይቱን የመሩት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አብዱላሂ አደን በበኩላቸው፣ የድሬዳዋ ነዋሪዎች ከአስተዳደሩ ጋር በመቀናጀት ለዘላቂ ሰላም፣ ልማትና መልካም እስተዳደር እያበረከቱት ያለውን አስተዋጾ ማጠናከር እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

አስተዳደሩ ከነዋሪው የተነሱ መሠረታዊ ጥያቄዎችን ቅደም ተከተል በመስጠት ለመፍታት በትኩረት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።


በከንቲባ አብዱላሂ አደን የተመራው የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራር ከህዝብ ውይይቱ በተጨማሪ የተለያዩ ወረዳዎችንና የሴክተሮችን የሥራ እንቅስቃሴዎች የተመለከተ ሲሆን ከአመራሮችም ጋር ውይይት አካሂደዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በኢሉባቦር ዞን ከቡና ምርት የሚገኘውን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በቡና ጥራት አጠባበቅ ላይ ትኩረት ተሰጥቷል

መቱ፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):- በኢሉባቦር ዞን ከቡና ምርት የሚገኘውን ገቢና የአካባቢውን አምራቾች ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ በቡና ጥራት አጠባበቅና...

Sep 23, 2026

በክልሉ ያለውን የውሃ ሀብት ለመስኖ ልማት በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ይገባል - ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለውን የውሃ ሀብት ለመስኖ ልማት በማዋል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት ተጠና...

Sep 18, 2026

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026