የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

ሕዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሁለንተናዊ የልማት ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ

Oct 9, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አርባምንጭ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሁለንተናዊ የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር )ገለጹ፡፡

የክልሉ መንግሥት በፍትሐዊነት ላይ የተመሠረተ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትን የማረጋገጥ ስራውን አጥናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) እና የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ከአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ዛሬ ውይይት አድርገዋል።


ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት መንግስት ትኩረት የሰጣቸው የኢኮኖሚ ምሶሶዎችን መሰረት በማድረግ የክልሉን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የሚያከናውናቸው ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ።

በዋናነት የመስኖ አውታሮችን በመገንባትና በመካናይዜሽን የታገዘ የእርሻ ስራዎችን እንዲስፋፉ በማድረግ ግብርናውን ከዝናብ ጥገኝነት ለማላቀቅ በተቀናጀ መንገድ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ለኢኮኖሚው የጀርባ አጥንት የሆኑ መሠረተ ልማቶችን በመገንባትና ተደራሽ በማድረግም የህዝቡን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል የሚያስችሉ ስራዎች እንደሚከናወኑም ነው ያረጋገጡት።

የሰላም ግንባታን በማጠናከርም የህዝቡን አንድነትና አብሮነት በማጎልበት ክልሉ የሰላም ተምሳሌት እንዲሆን በላቀ ትጋት እንደሚሰራ ነው የጠቆሙት ።

የሌማት ትሩፋትን ጨምሮ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጀመሩ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን በማጠናከርም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና የስራ ዕድል ለመፍጠር በልዩ ትኩረት ይሰራል ብለዋል።

የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች በበኩላቸው የክልሉ መንግሥት በፍትሐዊነት ላይ የተመሠረተ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትን የማረጋገጥ ስራውን አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ነው ያመለከቱት።

በክልሉ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የሰላም እሴቶችን በመገንባት፣ አንድነትና አብሮነትን በማስቀጠልም ለሀገር ግንባታ ማዋል እንደሚጠበቅበት ነው የጠቀሱት።

በተጨማሪም መንግስት የአርባምንጭ ዓለም አቀፍ ስታዲየምን ጨምሮ በሁሉም አካባቢዎች የተጀመሩ የኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማቶች አጠናክሮ በመቀጠል ተጠቃሚነታችንን ሊያጠናክር ይገባዋል ብለዋል።

የመንገድ፣ የኤሌክትሪክ እና የዲጂታል መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋትም የከተሞችንና የገጠር ትራንስፎርሜሽን ለማፋጠን የሚከናወኑ ተግባራትም የተሻለ ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ አስረድተዋል።

የትምህርት፣ የጤና እና ሌሎች ማሕበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን በማጠናከር የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶች በልዩ ትኩረት እንደሚከናወኑም ያላቸውን ተስፋ ተናግረዋል።

በመድረኩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ምሁራንና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በኢሉባቦር ዞን ከቡና ምርት የሚገኘውን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በቡና ጥራት አጠባበቅ ላይ ትኩረት ተሰጥቷል

መቱ፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):- በኢሉባቦር ዞን ከቡና ምርት የሚገኘውን ገቢና የአካባቢውን አምራቾች ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ በቡና ጥራት አጠባበቅና...

Sep 23, 2026

በክልሉ ያለውን የውሃ ሀብት ለመስኖ ልማት በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ይገባል - ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለውን የውሃ ሀብት ለመስኖ ልማት በማዋል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት ተጠና...

Sep 18, 2026

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026